Telecommunication Equipment

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ሞባይል ቀፎዎች እና የተለያዩ ቴሌቪዥን ዕቃዎች በኦንላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ኦንላይን የግልጽ ጨረታ ቁጥር AE01/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ ኦንላይን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መስረት፡- በግልጽ ጨረታ ቁጥር AE01/2019 በ04/01/2019

  • የተለያዩ ሞባይል ቀፎዎች፤
  • የተለያዩ ቴሌቪዥን ዕቃዎች በኦንላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

  1. በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣  የተጨማረ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥርን ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላዶ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድእነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
  3. በግልጽ ጨረታው ሳይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ እና የዕቃዎቹን ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡ እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ  ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  4. ጨረታው የሚካሄደው ሙሉ ለሙሉ በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ነው።
  5. ለግልጽ ጨረታ በሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
  6. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፋ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው በእያንዳንዱ ምድብ የሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (CuSTOMS COMMISSION DIREDAWA BRANCH OFFICE) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሠራት ያሠሩትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ግልጽ ጨረታ ኦንላይን ከሆነበት ከ30/12/2018 ዓ.ም 4:00 ጀምሮ እስከ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 04/01/2019 ዓ.ም 4፡00 መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል።
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ይሆናል።
  9. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
  10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላዶ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
  11. የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ የጥሪ ማዕከሉን ስማገኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0915460970(0912885746) መደወል ይቻላል

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-14 10:00
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ministry of Customs Diredawa Branch Bureau
  • Bid bond: በእያንዳንዱ ምድብ የሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%)
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T08:53:47.000Z
← Back to all tenders