Textile, Garment and Leather
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በኦክሸን ኢትዮጵያ (auction Ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በ04/03/2009 ዓ/ም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ በኦክሸን ኢትዮጵያ (auction Ethiopia) መተግበሪያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መተግበሪያውን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር auction Ethiopia ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብና የጨረታ ሰነዱን በማየት፣ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፡ የእቃዎችን ሳምፐልም ከኦክሸን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ (auction Ethiopia pape) ወይም አዋሸ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ወይም በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች፡
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፡ ዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ04/03/2019 ዓ/ም ከኦክሽን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ (action Ethiopia page) ማየት ይችላሉ።
4. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ በሲስተም አታች ማድረግ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
አጫራች ቅ/ጽ/ቤት |
የጨረታው ዓይነት |
ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀን ሰዓት |
|
1 |
አዋሸ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት |
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ |
ጫማዎች አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነፅር ጌጣጌጥ፣ የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ ተሽከርካሪ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ04/03/2019 ከሰዓት 9፡45
|
ግልጽ ጨረታ መዝጊያ በ04/3/2019 ዓ/ም ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ04/03/2019 ዓ/ም 11፡00 ሰዓት ይሆናል። |
5 የጨረታው መክፈቻ ሰዓት እና ቀንን ከኦክሸን ኢትዮጵያ ድህረ-ገጽ auction Ethiopia page በማየት የጨረታው ሂደት ተጀምሮ ከማለቁ በፊት ዋጋ መስጠት ይችላሉ፡፡
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል::
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያ ያስያዙት ገንዘብ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሸያጭ ይቀርባል፡፡
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10 የኦክሽን ኢትዮጵያ(auction Ethiopia) መተግበሪያን በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ሠራተኛ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 09-05-11-55 11/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-13-97-49-27 ይደውሉ ፡፡
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-13
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-11-13 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Afar
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T08:32:58.000Z
- Source: Qelal Tenders