Building and Finishing Materials

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ ቆርቆሮ፣ LTZ፣ መስታወት፣ ፑቲ፣ ሚስማር፣ ሲሚንቶ እና ተመሳሳይ የግንባታ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2019 

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ

ሀ/ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን ማለትም

1. ቆርቆሮ LTZ፣ መስታወት ፣ ፑቲ ፣ ሚስማር ፣ ሲሚንቶ እና ተመሳሳይ የግንባታ ዕቃዎችን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10000.00 በማስያዝ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱ እቃዎችን ዋጋ ቫትን አካቶ በመሙላት ኮሌጁ ለዚሁ ሥራ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ለ በዚሁ መሰረት

  1. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በ(VAT) ከፋይነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  3. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም፣
  4. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሣተፉባቸው ዕቃዎች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ከላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፣
  7. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  8. ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ድርጅት ከፍያ የሚፈጽመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ
  9. ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቧቸውን ሠነዶች ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የግልጽ ጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ/ም በማለት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በ 16 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።
  11.  የጨረታው አሸናፊ ድርጅት በጨረታው ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውም ወጪ የጉምሩክ ቀረጥን ጨምሮ በመሸፈን ዕቃዎቹን የሚያስረከበው ዲላ ትም/ ኮሌጅ ነው።
  12. ተጫራቾች ለጨረታ በሠነድ ላይ ያቀረቡት ዋጋ ላሸነፉባቸው ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እስከሚያስረክቡበት ጊዜ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል ።
  13.  ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በማስያዝ ከመሥሪያ ቤቱ ጋር የሽያጭ እና የግዥ ውል ይፈራረማሉ።
  14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የዕቃዎቹን አይነት ፣ የአምራቹን ስም ፣ የተመረተበትን ሀገር ፣ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበትን ዓመት ጭምር ማካተት ይኖርበታል። የእስፔስፊኬሽን መግለጫ የሚያስፈልጋቸው እቃዎች በአይነት በፎቶና የአቅም መለያ እንደአማራጭ ይቅረብ።
  15. ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፣
  16. የዕቃው ርክክብ አሸናፊ ከሆነው ድርጅት ጋር የሚከናወነው የግዥው መሥሪያ ቤት ባለሙያዎች በሚያደርጉት የጥራትም ሆነ የዓይነት ምርመራ በ /Specification/ መሠረት ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ ይሆናል፣
  17.  የጨረታ ሰነዱን ከዲላ ትምህርት ኮሌጅ ብር 100 በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር በግዥ ማግኘት ይችላሉ።
  18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ እንዲሁም ብዛት የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ ስ.ቁ 046-331-36-29

የዲላ ት/ኮ/ግ/ፋ/ን አስተዳደር ስ.ቁ 046331-42-51

ፋክስ  046-331-24-92

የዲላ ትምህርት ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በ16 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-21 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በ16 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Dilla Education College
  • Bid bond: ብር 10000.00
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T09:12:25.000Z
← Back to all tenders