Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1 የፅህፈት ዕቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት 3 ልዩልዩ እቃዎች ሎት 4 የደንብ ልብስ ሎት 5 የቋሚ እቃዎች ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 7 የሕክምና እቃዎች ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሎት 9 የትምህርት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO. ማቅረብ አለበት።
ሎት ቁጥር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር
- ሎት 1 የጽህፈት እቃዎች ብር 74000
- ሎት 2. የፅዳት እቃዎች ብር 68000
- ሎት 3 ልዩልዩ እቃዎች ብር 20000
- ሎት 4 ደንብ ልብስ ብር 60000
- ሎት 5 ቋሚ እቃዎች ብር 28000
- ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 30000
- ሎት 7 የህክምና ዕቃዎች ብር 10000
- ሎት 8. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ብር 29000
- ሎት 9 የትምህርት ዕቃዎች ብር 33000
የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
6. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
10. የጨረታ አሽናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪያቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።
11. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. መ/ቤ/ቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ስልክ፡- 011 868 1536 / 011 868 1537
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ መሪ ገበያ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-16
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-16 14:30
- Bid opening (note): ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Lemi Kura Sub City Woreda 10 Meri Elementary School
- Buyer address: በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ መሪ ገበያ 500 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T09:25:15.000Z