Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 እውቀት ለፍሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት ለመስሪያ ቤቱ ስራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 እውቀት ለፍሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት ለመስሪያ ቤቱ ስራ አገልግሎት የሚውሉ፡
|
የሎት አይነት |
ሎቱ የሚወክለው ዘርፍ |
ለየሎቱ የሚያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ መጠን |
|
ሎት 1 |
የፅፈት መሳሪያ |
15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 2 |
የደንብ ልብስ |
15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 3 |
የፅዳት እቃ |
5000 /አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 4 |
ኮምፒውተርና ፕሪንተር ተዛማጅ |
15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 5 |
ፈርኒቸር ሌሎች ቋሚ እቃዎች |
10000 /አስር ሺህ ብር/ |
|
ሎት 6 |
መፅሃፍት |
5000 /አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 7 |
የህክምና እቃዎች |
1000 /አንድ ሺህ ብር/ |
|
ሎት 8 |
የተለያየ የማሽን ጥገና ስራ |
1000 /አንድ ሺህ ብር/ |
|
ሎት 9 |
የጀነሬተር ጥገና |
የለውም |
|
ሎት 10 |
የተለየዩ ኬሚካሎችን ማሶገድ |
የለውም |
|
ሎት 11 |
የጥገና ስራ |
5000 /አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 12 |
መኪና ኪራይ |
የለውም |
በጨረታ ቁጥር 01/019 አወዳድሮ እቃዎቹን እና አገልግሎቶቹን ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በጨረታው እንዲሳተፍ ይፈልጋል።
1. ከላይ በዝርዝር ለተጠቀሱት ዕቃዎች አግባብነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም አዲስ አበባ መስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ በዕውቀት ለፍሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ለሙሉ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚዘጋው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ተዘግቶ 5፡00 ይከፈታል።
4. ተጫራቾች እያንዳንዱ ዕቃ እና አገልግሎት የሚሸጡበትን ዋጋ ከነቫቱ መግለጽ አለባቸው።
5. በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች እና ከተቋሙ የሚገዙትን ሰነድ ጭምር ኦርጅናሉን ኮፒ በማድረግ በ2 በተለያዩ ፖስታዎች አስገብቶ አርጅናልና ኮፒ ብሎ በመፃፍና በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ሰነዱ ላይ በመፈረም ማህተም በመምታት በዕውቀት ለፍሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረት ቤት በግዢ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ በሚሞሉበት ጊዜ ስተት ከተፈጠረ በአንድ መስመር ሰርዞ ካናቱ ፌርማ በማድረግ ማስተካከል ይፈቀዳል ነገር ግን በፍሉድ ማጥፋት እና ስርዝ ድልዝ ማድረግ አይፈቀድም።
7. ተጫራቹ ዋጋ መሙላት ያለበት በተቋሙ ሰነድ ላይ ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ ሌላ ሰነድ መጠቀም አይፈቀድም።
8 ከተቋሙ ፍላጎት ወይም ስፔሲፊኬሽን ውጪ በራስ ፍላጎት ማርክ ጠቅሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
9 በሰነዱ ላይ ዋጋ በሚሞሉበት ወቅት የማይወዳደሩበትን እቃ ዋጋ መሙያ ቦታውን ባዶ መተው አይፈቀድም።
10. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ በተጨማሪም መደበኛ የጨረታ ሰነዱን በተጫራች የሚሞሉትን እና መፈረም ያለባቸውን ቦታዎች በአግባቡ ሞልቶ ፈርሞ መሃተም አድርጎ መመለስ አለባቸው
11 በጨረታ ለቀረቡት እቃዎች ሳምፕል የሚገቡ እቃዎች የማወዳደሪያ ሰነዱ ላይ ተጠቅሰዋል ናሙና መቅረብ ያልቻሉ እቃዎችን ከውጤት በኋላ በአካል ይዞ በመምጣት ማሳየት እና ትዛዝ ሲሰጠው ማስገባት ይኖርበታል።
12. ከላይ በተጠቀሰው መሰረት CPO በልደታ ክፍለ ከተማ እውቀት ለፍሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
13. አሸናፊ ለሚሆኑ ተጫራቾች የውሉን 10 በመቶ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
14. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የሚወዳደሩትን የሎት መጠን ያክል ደምሮ በአንድ ሲፒኦ ማሰራት ይቻላል። መ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አምራች ካልሆኑ በስተቀር በደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- የቀድሞ 3 ቁጥር ማዞሪያ ቶታል ስልክ 011-8346370
ልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ቅ/ጽ/ቤት እውቀት ለፍሬ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-17
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት
- Bid opening: 2026-09-17 11:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 5፡00 ሰአት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Eweket Lefere Secondary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Lessan (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T09:46:53.000Z
- Source: 2merkato