Building Construction
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ አሰላ በሚገኘው ይዞታው ላይ የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የከብት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን መጋዘን ለማሰራት ሰነድ ላይ ባለው የሥራ ዝርዝር እና ቅድመ ሁኔታዎች (Evaluation Criteria) መሰረት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ኮንትራክተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ አሰላ በሚገኘው ይዞታው ላይ የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የከብት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን መጋዘን ለማሰራት ሰነድ ላይ ባለው የሥራ ዝርዝር እና ቅድመ ሁኔታዎች (Evaluation Criteria) መሰረት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ኮንትራክተሮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል።
1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ/ የህንፃ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ/ ፍቃድ ያለው።
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል (የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የስራ ቀናትን ከሰኞ - አርብ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን።)
3. ተጫራቾች በዚህ የንግድ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን ፣ቫት ፣ የንግድ መዝገባ ኮፒዎችን በማህተብ በማረጋገጥ እና ሰነድ ይሸጥልኝ ማመልከቻ ጋር ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ቴክኒካል ኦርጅናሉ ሠነዱ ጋር በማቅረብ መጫረት የሚችል።
5. ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት በ22ኛው ቀን ሲሆን 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል።
6. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ /ተጫራቹ ጥሩ የመልካም ስራ አፈፃፀም ሪከርድ ከሌለው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
7. ተጨማሪ ማብራሪያ ከድርጅቱ መረዳት ይቻላል።
አድራሻ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጀሞ ሚካኤል አጠገብ የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ ዋና መ/ቤት “OACF Buiiding" ላይ 6ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 12
ስልክ ቁጥር፡- 09 66 79 50 79 / 09 10 64 54 42
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሸን ኃ/የተ
Tender details
- Deadline: 2026-09-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-26 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Agricultural Cooperatives Federation
- Buyer address: ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከጀርመን አደባባይ ወደ ጀሞ ሚካኤል በሚወስደው ቀለበት መንገድ ላይ አድማስ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት ፎቅ አጠገብ ሁለተኛ ፎቅ
- Bid bond: 500,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T09:48:53.000Z
- Source: 2merkato