Stationery
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጽህፈት መሳሪያ እና ሞተር ሳይክል ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
Central Ethiopia
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት መደበኛ በጀት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፦ የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት 2፦ ሞተር ሳይክል
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- የዕቃው አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዕቃዎቹን እስፔስፊኬሽን በተገለፀው መሰረት ተሞልቶ እንዲገለጽና ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የም/ጉ/ዞ/ፋ/መምሪያ በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 10,000/አስር ሺህ/ እና ለሎት 2 ብር 10,000/አስር ሺህ/ ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተመሰከረለት/CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጁት ዝርዝር እስፔስፊኬሽን ላይ ሞልተው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን የምስ/ጉ/ዞን ፋይናንስ ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይጠበቅበታል። መስርያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 16 83 97 98 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-21 10:30
- Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: East Guraghe Zone Finance office
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T09:57:43.000Z