Stationery

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 001/2019

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት፡-

ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. አላቂ የፅህፈት እቃዎች፣ ሎት 3. አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 4 ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 6. ህትመት፣ ሎት 7. መድሃኒት እና ሪኤጀንት፣ ሎት 8. የአልሙኒየም ፓርቲሽን ስራ (አቅርቦትን ጨምሮ) ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጨራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃማ ቅረብ የሚችል፣

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

3. የታደሰ የንግድ ፍቃድያለው፣

4. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቁባቸው እቃዎች ናሙናውን ቀድመው ጨረታ ሰነዱ ሣጥን ውስጥ ከማስገባታቸው በፊት ማቅረብ አለባቸው።

5. የቋሚ እቃ ተጫራቾች በአድራሻችሁ በመምጣት የእቃዎችን እስፔክ እና ጥራት የምናይ ይሆናል።

6. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

7. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

     ሎት ቁጥር የሎት ዝርዝር  የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ

  • ሎት 1. የደንብ ልብስ  .የኢትዮ.ብር 15,000
  • ሎት 2. አላቂ የፅህፈት እቃዎች .የኢትዮ.ብር 15,000
  • ሎት 3. የፅዳት እቃዎች .የኢትዮ.ብር 10,000
  • ሎት 4. ቋሚ እቃዎች የኢትዮ.ብር 30,000
  • ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች አላቂ የቢሮ እቃዎች የኢትዮ ብር 8,000
  • ሎት 6. ህትመት .የኢትዮ.ብር 15,000
  • ሎት 7. መድሃኒት እና ሪኤጀንት .የኢትዮ ብር 30,000
  • ሎት 8. የአልሙኒየም ፓርቲሽን ስራ (አቅርቦትን ጨምሮ).የኢትዮ ብር 30,000

8. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 404 /4ኛ ፎቅ እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።

9. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሠዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የገንዘብ መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ cpo ማስያዝ አለባቸው።

12. ተጫራቾች ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው። ስፔስፊኬሽን ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማ መኖር አለበት።

13. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

14. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበ ውዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ተጫራቾች በሰነዳቸው ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም መረጋገጥ አለበት።

አድራሻ፡- ስልክ 09-86-38-96-18 /0118 88 01 28

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ከማርያም ማዞሪያ 100 ሜ ገባ ብሎ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር የቦሌ ቡልቡላ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Bulbula Woreda 12 Health Post
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Lessan (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T10:02:39.000Z
← Back to all tenders