Stationery

በልደታ ክ/ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት ካራማራ የመጀ/ደረጃ፣ ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ እና ቀበሌ 37 ቅ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክ/ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት ካራማራ የመጀ/ደረጃ፣ ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ እና ቀበሌ 37 ቅ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሎት በዝርዝር የተገለፁትን ዕቃዎች፣ ሎት1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት3 የደንብ ልብስ፣ ሎት4 አላቂና ቋሚ የት/ት መርጃ ዕቃዎች፣ ሎት5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት6 የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸር መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት7 የተለያዩ የህትመት ስራዎች ሎት8 የመስተንግዶ ውሃ እና ቆሎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት

2. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ

3. በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት

4. የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት እና የዘመኑ ግብር የከፈላችሁበት ሰነድ ማቅረብ የምትችሉ ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ( የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን እንዲሁም በዋጋ መሙያው ላይ ሳፕል እንዲቀርብባቸው የተገለፁትን ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን በሎት6 የተገለፀውን ዕቃ በማምረቻ ወይም በመሸጫ ቦታችው ማሳየት ያለባቸው መሆኑን እያሳውቅን ለዚሁ

ጨረታው ማስከበርያ የሚሆን ለሎት1.12000.00 /አስራ ሁለት ሺ ብር/፣ ሎት2.10000.00 /አስር ሺ ብር/፣ ሎት3.10000.00 /አስር ሺ ብር/፣ ሎት4.10000.00 /አስር ሺ ብር/፣ ሎት5.15000.00 /አስራ አምስት ሺ ብር/፣ ሎት6.10000.00 /አስር ሺ ብር/ ሎት7. 3000.00/ ሶስት ሺ ብር/ ሎት8. 2000.00 /ሁለት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በሁለት ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ት/ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ት/ቤቱ ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ዋጋችሁን በመሙላት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰነዳችሁን በማስገባት መወዳዳር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የጨረታ ሰነድ በደብዳቤ የምናስተናገድው አምርታችሁ ለገበያ በምታቀርቡት ምርት ላይ ብቻ ነው።

ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት /አስራ አንድ ሰዓት/ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ሲከፈት የማይገኙ ተጫራቾች ጨረታው በሌሉበት እንደሚከፈት እያሳወቅን የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡- ት/ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የምታቀርቡት ናሙና (ሳምፕል ) ላይ የድርጅታችሁን አርማ ማሃተም ማድረግ አይቻልም!!

አድራሻ፡- በልደታ ክ/ከ/ወ/03 ካራማራ የመጀ/ደ/ት/ቤት አብነት አደባባይ ጆስሀንስን አጠገብ ስልክ ቁጥር 0112-73-23-45
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ካራ ማራ የመጀ/ደረጃ፣ ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ቅድመ አንደኛ እና ቀበሌ 37 ቅ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በልደታ ክ/ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት ካራማራ የመጀ/ደረጃ፣ ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ እና ቀበሌ 37 ቅ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Lessan (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T10:19:28.000Z
← Back to all tenders