Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ
- የፅህፈት መሳሪያዎች
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣
- ቋሚ ዕቃዎች እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችን ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ከሚችሉ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው : የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ደሴ ከተማ ፡ ከመናፈሻ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50/ አምሳ ብር / በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በመሙላት ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በማድረግ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ፖስታውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 2፡30 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት በቀጣዩ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ በማስቆረጥ ከኦሪጅናል የዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ደሴ ከመናፈሻ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር +251333120912
በመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 2፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-15 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Government Organization's Employees Social Security Agency North East Region Office
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 50.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T10:19:54.000Z