Stationery

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 01/2019 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ስለሆነም ተጨራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል እቃዎች እና አገልግሎት በግዥ መለያ ቁጥር 01/2019 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1 በዘርፉ የተሰማራበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ መረጃ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (Tin)ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ማስረጃ ያላቸው

2. የጨረታ ማስከበሪያ CPO በባንክ የተረጋገጠ በየሎቱ

  • ሎት- 1 የፅህፈት መሳርያ 40,000፣
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ 40,000፣
  • ሎት-3 የጽዳት እቃዎች 35,000፣
  • ሎት-4 የህትመት ስራዎች 5,000፣
  • ሎት 5 የጓሮ አትክልት ዘር ግዥ 1,000
  • ሎት 6 የእንስሳት ህክምና አላቂ እቃዎችና መድሃኒቶች 1,000፣
  • ሎት 7 ትራንስፖርት አገልግሎት 5,000፣
  • ሎት-8 ለቢሮ መስተንግዶ 2,000፣
  • ሎት-9 እንጨት ነክ እድሳትና ጥገና 1,000
  • ሎት 10 የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች ግዥ 30,000
  • ሎት 11 የልብስ ስፌት 1,000
  • ሎት 12 የጭነት የጉልበት አገልግሎት ከተደራጁበት መ/ቤት ደብዳቤ በማፃፍ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወረዳ 10 ለፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ናሙና በተጠየቀባቸው እቃዎች/ሎቶች ላይ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙናው መግባት ይኖርበታል።

4. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳው አዳራሽ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ዋጋውን ከቫት ጋር ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

6. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

7. አሸናፊ ተጨራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

* ለተጨማሪ መረጃ፡- ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ሳሪስ ኢካፍኮ 100 ሜትር ገባ ብሎ የወረዳ 10 አስተዳደር  ህንፃ ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው የስራ ቀን ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nifas Silk Lafto Sub City Wereda 10 FEDB
  • Buyer address: ሳሪስ ኢካፍኮ 100 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 200 /ሁለት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T10:37:24.000Z
← Back to all tenders