Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ እቃዎች እና ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል
More tags
Description
የ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ የካ ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት መገልገያ የሚውሉ መድሃኒት፣ የደንብ ልብስ፣ የፅህፈት እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የህትመት ስራዎች፣ የጥገና እቃዎች የቢሮ እቃዎች፣ የምግብ ግብአቶች እና የጥገና ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ተጫራቾችን መጋበዝ ይፈልጋል።
በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
- በየሎት 1 የደንብ ልብስ- 10000 ብር
- 2. የፅህፈት እቃዎች 5000
- 3. የፅዳት እቃዎች 5000
- 4. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 15000 ብር
- 5. ለኮምፒውተር ና ተዛማጅ እቃዎች 10000 ብር
- 6. የደንብ ልብስ ስፌት 2500 ብር
- 7. የህትመት ስራዎች 10000 ብር
- 8. የጥገና እቃዎች 10000 ብር
- 9. የቢሮ እቃዎች 10000 ብር
- 10. የምግብ ግብአቶች 1000ብር
- 11. ጥገና ስራዎች 7000 ብር
- 12.መድሃኒት -10,000 ብር
በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (CPO) በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈራረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በየካ ጤና ጣቢያ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ ቡድን በመገኝት ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
7. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ስርዙ ጎን ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል።
9. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ7 የስራ ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖረበታል።
10. አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
11. ጤና ጣቢያው የአቅርቦት ዝርዝር (ስፔስፍኬሽን) በሚጠይቁ አቅርቦቶች ላይ ባወጣው መሰረት ተጫራቾች ካታሎግን ጨምሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
12. የጨረታም ሆነ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አሸነፋችሁም አላሸነፋችሁም ከ6ወር በፊት መውሰድ ይኖርባችዋል 6ወር በኋላ የሚወረስ መሆኑን እናሳውቃለን።
13. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንግድ የሚያጋጥመው ከሆነ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦- የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፊት
ለፊት ስልክ ቁጥር፡- 011 893 29 82/011 667 42 37
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
የካ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-18 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yeka Sub City Yeka Health Post
- Buyer address: የካ ጤና ጣቢያ ሾላ ገበያ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T08:17:35.000Z
- Source: 2merkato