Stationery
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የጽሕፈት እና የቋሚ ዕቃዎች፣ የሞተር ጎማ፣ የቢሮ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase
Oromia
More tags
Spare Parts and Car Decoration MaterialsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsOffice FurnitureFurniture and FurnishingComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesAmharic2merkatoEast Harage Zone High Court
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ የጨረታ መለያ ቁጥር 1 /2019
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የጽሕፈት እና የቋሚ ዕቃዎች የሞተር ጎማ የቢሮ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆንም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት የሥራ መስክ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ኮፒ አባሪውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና ለሚያወዳድሩባቸው ዕቃዎች ዋጋ ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ያዘጋጁትን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ኦፕሬሽን ግዢ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማክበሪያ ዋስትና የሚያስይዙት የጨረታውን ዋጋ 2% በፎርሙላ ቅፅ ሲፒኦ (CPO) በማዘጋጀት ማቅረቢያውን ከመዝጋታቸው በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በግልፅ በማስቀመጥ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉን በደብዳቤ ከተገለጸለት በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያ ካስያዘው 10% በማስያዝ ወይም የተመረጡትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ካስረከበ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለስለታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሐሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከከፍተኛው ፍ/ቤት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 87 (ሰማንያ ሰባት) በግልፅ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የናሙና ዝግጅት ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ናሙና ማቅረብ አይቻልም፤ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የሚያ ቀርቧቸው ዕቃዎች በጥራት ደረጃቸው ጥሩ መሆን ያለባቸው ሲሆን ዋስትና ማቅረብ አለባቸው::
- የማጓጓዣ እና የጭነት ወጪ በተጫራቾች ይሸፈናል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- አድራሻ ወረዳ በኢሊዩ መንገድ ሐረርጌ ከፍተኛ ፍ/ቤት
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሂደት
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-18 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: East Harage Zone High Court
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T08:38:52.000Z
- Source: 2merkato