Stationery
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesOffice Machines and Accessories
Addis Ababa
More tags
Computer and AccessoriesIT and TelecomEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureFinishig WorksConstruction and Water WorksOthersMaintenance and RepairOffice Machines and ComputersFurnitureCatering and Cafeteria ServicesPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsSpare Parts and Car Decoration MaterialsTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseHouse and BuildingVehicle (garage service)Amharic2merkatoLedeta Sub City Small Tax Payers Branch Office
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ልደታ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት አንድ: የተለያየ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት: ቋሚ እቃዎች
- ሎት ሦስት: የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት አራት፡- የተለያዩ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- ሎት አምስት: የቢሮ መገልገያ እቃዎች ጥገና እና ፓርትሽን ሥራ
- ሎት ስድስት: የመስተንግዶ ግዥ
- ሎት ሰባት ፡- የህትመት ስራዎች
- ሎት ስምንት: የደንብ ልብስ
- ሎት ዘጠኝ: የመኪና እቃዎች
- ሎት አስር: የሞተር ሳይክል ጥገና
- ሎት አስራ አንድ: የአይቲ እቃዎች
- ሎት አስራ ሁለት: የፕሪንተሮች መለዋወጫ እቃዎች
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል.
- ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ጋር ተዛማጅ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ እና የጨረታ መወዳደሪያ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- የአገር ውስጥ የግብዓት አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ካላቸው ማቅረብ የሚችሉ እና የጨረታ ማስከበሪያ ለአንድም ሆነ ለሁሉም ሎቶች ብር 20,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: CPO መሠራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6:00 ሰዓት ድረስ ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር በሚወስደው መንገድ ተወልደና ልጆቹ ህንጻ ላይ ልደታ ክ/ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ከግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6ኛ ፎቅ 602 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::የሚያቀርቡት ዋጋ ታክሱን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ ማቅረብ አለባችሁ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3:30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት 6ኛ ፎቅ 603 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል።
- ሰነዱን በሚመለስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት።
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- የጨረታው አሸናፊ ሲረጋገጥ አሸናፊው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ከቋሚ እቃዎች እና የህትመቶች ውጤቶች በስተቀር ሌላው ሁሉም ናሙና መምጣት የሚችሉ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችን ማስረከብ አለባቸው ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ መወዳደር አይችልም ፖስታ ሳይከፈት ውድቅ ይደረጋል።
- የፕሪንተር ቀለም ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት ቀለም አይነት ስለጥራቱ የ6 ወር የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር 0115-50-99-37
ስልክ ቁጥር 0115-57-25-84
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-18 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ledeta Sub City Small Tax Payers Branch Office
- Buyer address: ለገሃር የቀድሞ ናዝሬት መኪና ተራ ፊት ለፊት ተወልደና ልጆቹ ሕንፃ ላይ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 ነው
- Bid bond: 20,000.00 ብር ለአንድም ሆነ ለሁሉም ሎቶች
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T09:29:59.000Z
- Source: 2merkato