Vehicle and Machinery Sale
ህብረት ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ቁጥር 002/2019
ህብረት ባንክ አ.ማ ይጠቀምባቸው የነበሩ ከዚህ በታች የተገለፁትን ብዛታቸው 10 (አስር) የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። (የተሽከርካሪዎቹ አይነት ከዚህ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ ይመልከቱ)
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
የሠሌዳ ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የተሽከርካሪው ሞዴል |
የተሰራበት ዘመን |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
Hyundai Grand i 10 |
3-A11180 |
MALA741CBFM044109 |
G4LA-EM385950 |
I10
|
2014
|
2,300,000.00
|
|
2 |
Automobile Nissan sunny |
3-95238 |
JNIBEANI6Z0001319 |
QG13-392307 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,400,000.00
|
|
3 |
Automobile Nissan sunny |
3-95239 |
JNIBEANI6Z0001314 |
QG13-392304 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,500,000.00
|
|
4 |
Automobile Nissan sunny |
3-78284 |
JNIBEANI6Z0001190 |
QG13-392167 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,500,000.00
|
|
5 |
Automobile Nissan sunny |
3-79720 |
JNIBEANI6Z0001320 |
QG13-392306 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,250,000.00
|
|
6 |
Automobile Nissan sunny |
3-79989 |
JNIBEANI6Z0001169 |
QG13-392109 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,450,000.00
|
|
7 |
Automobile Nissan sunny |
3-89252 |
JNIBEANI6Z0001182 |
QG13-392161 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,350,000.00
|
|
8 |
Automobile Nissan sunny |
3-82446 |
JNIBEANI6Z0001181 |
QG13-392160 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,500,000.00
|
|
9 |
Automobile Nissan sunny |
3-82445 |
JNIBEANI6Z0001183
|
QG13-392158 |
BDEALMFN16EHAD-B |
2011 |
1,400,000.00
|
|
10 |
Automobile Nissan sunny |
3-75915 |
JNIBEANI6Z0000488
|
QG13-391475 |
SUNNY SALOON
|
2010
|
1,200,000.00
|
በመሆኑም
1. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ሜክሲኮ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት (ህብር ታወር ሕንጻ) ዘወትር ሰኞ፣ ረቡዕ አና አርብ ጠዋት 3፡30 እስከ 5፡30 እንዲሁም ከሰዓት 8፡00 እስከ 10፡00 ድረስ በአካል በመገኘት መጎብኘት ይችላሉ።
2, ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል መጫረት የሚፈልገውን ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም 25% በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ አለበት።
3. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በአካውንት ቁጥር IN0403007 አቅራቢያቸው በሚገኝ በማንኛውም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከባንኩ ህብር ታወር ህንጻ 4ተኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተ.እ.ታን የሚያካትት ወይም የማያካትት ስለመሆኑ በግልጽ ማስፈር የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህን ሳይገልጹ ቢቀር ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ባንኩ 15% ተ.እታን በመጨመር የሚያወዳድር ይሆናል።
5. ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ሽያጩ ከፀደቀ በኋላ የሚመለስላቸው ሲሆን የጨረታው አሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙት ገንዘብ ለሚገዙት ንብረት ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ይታሰብላቸዋል።
6. በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊ መሆነ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ቀሪውን የሽያጩን ገንዘብ በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል የሚጠበቅበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ቀን ካልፈፀመ ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
7. ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ሕብር ታወር 4ኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት በዋናው መስሪያ ቤት 4ተኛ ፎቅ በሠራተኞች ካፍቴሪያ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ባንኩ ንብረቶቹን በገዢው ስም ለማዘዋወር ለሚመለከታቸው መንግስታዊ አካላት ደብዳቤ ይጽፋል።
10. የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዘ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያች ማለትም ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎችና ሌሎች ገዥ አንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል።
11. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 562 1024 ወይም 011 416 9757 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
ሕብረት ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-09-22 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hibret Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T12:05:32.000Z
- Source: 2merkato