Vehicle and Machinery Sale

አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ /አማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን እና በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከተውን ተሽከርካሪ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንኮች በተሰጠዉ ስልጣን መሠረት ንብረቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን ¼  (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል።
  3. ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀን እና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
  4. የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር ፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል።
  5. ተሽከርካሪውን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል።
  6. በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
  7. የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ኢማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ B 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የፎርክሎዠርና ዴት ሊቲጌሽን ዲቪዥን ለጨረታ ባዘጋጀው ክፍል ውስጥ ነው።
  8. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 0711 ወይም 011 515 1153 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የተበዳሪው ስም

የመያዝ ሰጪው ስም

የተሸከርካሪው ዓይነትና የተሰራበት ዘመን

የሰዳ ቁጥር

 

ንሲ ቁጥር

 

የሞተ ቁጥር

 

የተከርካሪዉ ሞዴል

 

የጨረታ መነዋጋ ብ

ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን

የምዝገባ

ሰዓት

 

የጨረታ

ሰዓት

 

አቶ ደመላሽ ታደሰ ዓሊ

ተበዳሪው

የመስክ ተሸከርካሪ (ጃፓን ቶዮታ / Toyota Landcruiser V8 VXR/) (እ.ኤ.አ 2013)

አአ-02-B78246

JTMHX05J2 E4061303

1UR0399671

URJ200L-

GNTNKV

12,141,740.00

 

መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም

4:30-5:30

5:30-6:00

 

 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-09-22 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
  • Posted at: 2026-09-07T14:35:07.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders