Stationery

በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ፈርንቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ሞተር ሣይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • የጽህፈት መሳሪያ፣
  • የጽዳት ዕቃዎች፤
  • ፈርንቸር፣
  • ኤሌክትሮኒክስ እና ሞተር ሣይክል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች(ድርጅቶች) ወይም ግለሰቦች።

  1. በመስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ቲን ሰርተፊኬት፣ ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ማንኛውም ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500(አምስት መቶ ብር) የኪ ወረዳ ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት የኪ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ነጠላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት እና በተራ ቁጥር 1 ላይ ያሉትን ማስረጃዎች ኮፒ በፖስታ 1 ኦሪጅናል እና 2 ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ በየኪ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  7. ተጫራች ድርጅቶች (ግለሰቦች) አሸናፊ ሆነው ሲገኙ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO /በጥሬገንዘብ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ያሸነፉበትን ዕቃዎች በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኪ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው የሚያስረከቡ ሲሆን ያሸነፉበትን ዕቃዎች ውል ገብተው ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆኑ ለውል ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በጨረታ ህግና ደንብ መሰረት ለሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወሰድ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ ጽ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ሊወስድ ይችላል።

ማሳሰቢያ፡-

  • መ/ቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • በዕቃ ጥራት ላይ ችግር ካጋጠመ የጨረታ አሸናፊ በራሱ ወጪ እና ኪሳራ የሚቀይር ይሆናል።
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድና ፖስታ ላይ ስም፣ፊርማ፣አድራሻ፣ማህተምና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
  • ተጫራቾች ያሸነፉበትን የዕቃ ናሙና የማቅረብ ግደታ አለባቸው።

በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-25
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 10:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Yeki Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T08:41:41.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders