Stationery

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የጉርሱም ወረዳ ፍ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የጽኅፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 1 /29

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የጉርሱም ወረዳ ፍ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የጽኅፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ ማላት ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸዉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሠርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉና ለሚወደደሩባቸዉ ዕቃዎች ከብር 10,000 ( አስር ሺ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚረጋግጥ ሕጋ ዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ።
  •  ተጫራቾች በጨረታዉ ያሸነፉባቸዉን ዕቃዎች በራሳቸዉ ትራንስፖርት ወደ መ ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም ሲፒኦ (CPO) በማዘጋጀት ማረጋገጫዉን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በግልጽ የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተዉ በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታዉ አሸናፊ ማሽነፋቸዉን በጽሑፍ የምንገልጽላቸዉ ሲሆን ለጨረታ አፈጻጸም ማስከበሪያ ለአሸነፉበት ዕቃ 10% በማስያዝና ዉል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ካላቀረቡ በግዥ ሕጉ መሠረት መ ቤቱ አቅራቢዉን ድርጅት ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ በጨረታዉ ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
  • ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸዉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የያዘ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ከመስሪያ ቤቱ ቀርበዉ መዉሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በሚገኙበት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 87 ( ቢሮ) በግልጽ ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸዉ ዕቃዎች ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት የካታሎግ ናሙና ማቅረብ አለባቸዉ፣ ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ናና ማቅረብ አይቻልም፤ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራች ከዉድድር ዉጪ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርባቸዉ ዕቃዎች በሙሉ ኦርጂናል ሆኖ ለዚህም ዋስትና ማቅረብ አለባቸዉ።
  • የማስጫኛ እና የማስወረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ ፦ ጉርሱም ወረዳ ፍ/ቤት ፉ/ቢራ
  • ስልክ ቁጥር 0910 175 603
  • በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የጉርሱም ወረዳ ፍ/ቤት

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጉርሱም ወረዳ ፍ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሂደት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-19 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Grusum Woreda Court
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T09:09:34.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders