Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና የአዲስ ፍሬ አ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 001/2019 ዓ.ም

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና የአዲስ ፍሬ አ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ የሰራተኞች ጥቅማጥቅምና የደንብ ልብስ ስፌት /የጨረታ ማስከበሪያ ብር 9000
  • ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000
  • ሎት 3 ለተለያዩ የህትመት ስራዎች /የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3150
  • ሎት 4 ለአላቂ የህክምና ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200
  • ሎት 5 ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች መግዣ, የጨረታ ማስከበሪያ ብር 9,737.31
  • ሎት 6 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች አና አቅርቦቶች/ የፅዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 24,500
  • ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2600
  • ሎት 8 ለፕላንት፣ ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1000
  • ሎት 9 ለፈርኒቸር የቢሮ ዕቃዎች ማስከበሪያ ብር 5000
  • ሎት 10 ለፕላንትና ማሽነሪ (ኤሌክትሮኒከስ) ጥገና ማስከበሪያ ብር 500
  • ሎት 11 ዉሃ አና ቆሎ አቅርቦት ለ1 ዓመት ማስከበሪያ ብር 677.52

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና አዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት በመቅረብ በማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ መግዛት ይችላል። እንዲሁም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች አምራች ለሆኑ የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣት በነፃ መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸዉ ሀ/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት/፣

ለ/ በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገበ፣ ሐ/ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል፣ መ/ ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ የአምራችነት መረጃ ማቅረብ የሚችል

3. በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን በሲፒኦ በኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና አዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት በማሰራት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በለው እስከ 11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ስዓት ብቻ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤትና አዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ት/ቤቱ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

6. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት የት/ቤቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታ ሳጥን በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ መምህራን ማረፊያ ይከፈታል። የጨረታው ቀን መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበትና ናሙናለሚያቀርቡባቸው የዕቃ ዓይነት ከመስሪያ ቤታቸው በቀረበው እስፔስፊኬሽንመሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የአዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ ብሎ ልዩ ስሙ ስላሴ ወፍጮ ቤት ገባ ብሎ ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0115-51-58-61/ 0118-68-56-98

በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት የኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤት እና አዲስ ፍሬ አንደኛ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-18 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ት/ጽ/ቤት የኦክስፋም ቅድመ አንደኛ ት/ቤት እና አዲስ ፍሬ አንደኛ/ደ/ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 250.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T09:32:25.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders