Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ለመስሪያ ቤቱ ለአገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችን እና እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ለመስሪያ ቤቱ ለአገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችን እና እቃዎችን በጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የእቃ ዝርዝር

CPO መጠን በብር

ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች

5000

ሎት 2 የፅዳት እቃዎች

5000

ሎት 3. ደንብ ልብሰ ግዥ

5000

ሎት 4 ደንብ ልብስ ስፌት

5000

ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ

10000

ሎት 6 ቋሚ የቢሮ እቃ

5000

ሎት 7 ቋሚ የህክምና እቃ

20000

ሎት8 አላቂ የህክምና እቃ

10000

ሎት 9 ልዩ ልዩ እቃዎች

3000

ሎት 10 ህትመት

5000

ሎት 11 ሽንት ቤት እና የእጅ መታጠቢያ ጥገና

3000

ሎት 12 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና

1000

ሎት 13 ቋሚ የህክምና እቃ እቃዎች ጥገና

2000

ሎት 14 የድንኳን ኪራይ

3000

በባንክ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በደብዳቤ የምትወዳደሩ ተጫራቾች በፅህፈት ቤቱ የበላይ ሀላፊ የተፈረመ ህጋዊ ደብዳቤ በማስያዝ መግዛት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

ስለዚህ የተጠየቁትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ለአንድ ሎት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር እና በተጨማሪ ቋሚ የህክምና እቃ ጨረታ ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከጤና ፅ/ቤት የተሰጠዉን ስፔስፊኬሽን መውሰድ ያለባችሁ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ2፡30-11፡15 የጨረታ ስነድ ገዝታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተጫራቾች ጨረታ ለመካፈል ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት

2. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ በየዘርፉ ያላቸው መሆን አለበት

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ቫት የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው

5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚረጋገጥ የምስክር ወረቀት ያላችው መሆን አለባቸው፡፡

6. የግብር ከፋይነት ቲን ሰርተፍኬት መቅረብ አለበት፡፡

7. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

8. ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልን እና ፎቶ ኮፒ በመለየት የሚወዳደርበትን የሎት አይነት በፖስታ ላይ መገለፅ አለበት፡፡ በተጨማሪ ቋሚ የህክምና ዕቃዎችን የምትወዳደሩ ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒክ መግለጫዎችን በተለያዩ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡ የሚወዳደርበትን ሎት በግልፅ በፖስታው ጀርባ ላይ ያልገለፀ ተጫራች አይስተናግድም(ውድቅ ይደረጋል)፡፡

10. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ በኮሚቴዎች ይከፈታል፡፡

  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ::
  • እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅታችሁ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  • መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • እያንዳንዱ ሰነድ እንደ አስፈላጊነቱ 20% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡

አድራሻ፡- ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ከአያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው መንገድ አያት ቁጥር 1 ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401

ስልክ ቁጥር 011 869 0779 / 0118 681 387 /

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 02 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-18 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Sub City Woreda 02 Health Post
  • Buyer address: ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ከአያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው መንገድ አያት ቁጥር 1 ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት 4ኛ ፎቅ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለአንድ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T10:16:30.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders