Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የፉሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ቋሚና አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፣ የሠራተኛ የደንብ ልብሶች እና የዳኞች የችሎት ልብስ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸሮች፤ መጋረጃ እና የቢሮ ምንጣፎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የፉሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ቋሚና አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፣ የሠራተኛ የደንብ ልብሶች እና የዳኞች የችሎት ልብስ ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸሮች፤ መጋረጃ እና የቢሮ ምንጣፎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዘርፉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላው የንግድ ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ወደ ስንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1064669901216 ገቢ በማድረግ (በመክፈል) ደረሰኙን በመያዝ ከፉሪ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የፋይናንስ እና ንብረት ግዥ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር) በፉሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በማሰራት ከሠነዱ ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

3. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ስም እና አድራሻ በማድረግ በድርጅቱ ስልጣን ባለው አካል ማህተም እና ፊርማ በማረጋገጥ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በፉሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የፋይናንስ እና ንብረት ግዥ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (VAT 15%) ተመዝጋቢ የግብር ከፋይነት (TIN NO)ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ (ቫትን 15% ) ያካተተ መሆን አለበት፡፡

5. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል፡፡

6. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው እስቶር ሆኖ እቃዎቹ ጥራቱን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16 (አስራ ሥድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታዉ ይከፈታል፡፡

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፉሪ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት

አድራሻ፡- በፉሪ ክፍለ ከተማ ወለቴ ኖክ አደባባይ ሰበታ መንገድ 100 ሜትር አለፍ ብሎ ጂኤም ፈርኒቸር ህንፃ ላይ ::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር: 011-38-05-230 / 011-38-05-081

በሸገር ከተማ የፋሪ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16 (አስራ ሥድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-24 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16 (አስራ ሥድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Furi Sub City Woreda Court
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T10:29:45.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders