Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡02/2019

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለፁት መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ፡-

  • ሎት 01. አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
  • ሎት 02. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 03. የህትመት አገልግሎት
  • ሎት 04. የደንብ ልብስ
  • ሎት 05. የድንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 06. ቋሚ ዕቃዎች
  • ሎት 07. ኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 08. የኤልክትሮኒክስ እና ጀኔሬተር ሰርቪስና ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 09. መድሀኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት
  • ሎት 10. የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች/Medical Equipment/
  • ሎት 11. የህንፃ ጥገና እና ማስፋፊያ ስራ ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢያዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን/TIN/፣ የቫት/VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ መወዳደር የሚችሉት በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ካደራጃቸው ተቋም ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1 10,500(አስር ሺህ አምስት መቶ) ፣ሎት2. 13,500(አስራ ሶስት ሺህ አምስት መቶ) ፣ ሎት3. 6800(ስድስት ሺህ ስምንት መቶ) ፣ ሎት4. 10,000(አስር ሺህ) ፣ ሎት5. 6000(ስድስት ሺህ) ፣ ሎት6. 36,500(ሰላሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ) ፣ ሎት7. 20,700(ሃያ ሺህ ሰባት መቶ) ፣ ሎት8. 4,500(አራት ሺህ አምስት መቶ) ፣ ሎት9. 25,000(ሃያ አምስት ሺህ)፣ ሎት10. 30,000(ሰላሳ ሺህ) እና ሎት11. 30,000(ሰላሳ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

4. አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል አብነት ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ ıፎቅ የግዥ ከፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቪሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአብነት ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ የግዥ ከፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት በአብነት ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ 2ኛ ፎቅ አደራሽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01፣ ለሎት 02፣ ሎት 04፣ ሎት 05፣ ሎት 06፣ እና ሎት 07 በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣ ሎት 03፣ ሎት 08፣ ሎት 09፣ ሎት 10 እና ሎት 11 በመ/ቤቱ የፍላጎት መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ለእያንዳንዱ እቃዎች ነጠላ ዋጋ ከቫት ጋር እና ጠቅላላ ዋጋ ከቫት ጋር ማስቀመጥ ይጠበቅባችዋል።

10. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፓርት ጤና ጣቢያው ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

12. መ/ቤቱ ለጨረታ ካቀረባቸው እቃዎች ውስጥ እስከ 20% ድረስ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው::

13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ

በስልክ ቁጥር፡- 011-273 4349 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡- ልደታ ክ/ከተማ አብነት ጤና ጣቢያ ከአብነት አደባባይ ፊት ለፊት ግቤ ህንፃ ጎን 100 ሜትር ገባ ብሎ

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-18 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lideta Sub City Health Bureau Abent Health Post
  • Buyer address: አብነት አደባባይ ጊቤ ሕንፃ አጠገብ 100 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T10:37:05.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders