Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ ወስጥ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌትሮኒክስ፣ የቋሚ እቃዎች (furniture) እና የደንብ ልብስ ለ2019 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአዶላ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማ ወስጥ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌትሮኒክስ፣ የቋሚ እቃዎች (furniture) እና የደንብ ልብስ ለ2019 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ቀርባቹ መወዳደር ትችላላችሁ::

1. ተጫራቾች በዚህ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ስለመሆናቸው ህጋዊ የታደሰ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን የመንግስት ግብር ስለመከፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው በአቅራቢነት የተመዘገቡና ስለ ቀድሞ መልካም አፈጻጸም መረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ ::

3. ተወዳዳሪዎች ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በመደበኛ የስራ ሰዓት የማይመለስ 900 (ዘጠኝ መቶ) ብር በመክፈል በአዶላ ወዩ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ከፍል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የግዥ ዋጋ 2% ያላነሰ ብር 50.000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) በአዶላ ወዩ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ CPO ወይም በባንከ የተረጋገጠ ከዋናው (Orjinal) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡ የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ ለተሸናፊ ተወዳዳሪዎች ያቀረቡትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን ጨረታውን ላሸነፉት የሚመለሰው ደግሞ የውል ማስከበሪያ በአዶላ ገንዘብ ጽ/ቤት ካስገቡ በኋላ ነው::

5. የፅህፈት መሳሪያዎች የጽዳት እቃዎች እና የደንብ ልብስ የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች በሰም በታሸገ ፓስታ (envelope) ዋናውን ና ኮፒውን ለያይቶ ይህን ማስታወቂያ ከታተመበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ጨረታው 15 የስራ ቀናቶች ከተጠናቀቀ በኋላ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በአዶላ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዶላ ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል ሆናም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡

6. የኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ እቃዎች ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ተጫራቾች በሰም በታሸገ ፖስታ (envelope) ዋናውን ና ኮፒውን ለያይቶ ይህ ማስታውቂያ ከታተመበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ጨረታው 15 የስራ ቀናቶች ከተጠናቀቀ በኋላ በሁለተኛው ወይም ከአንድ ቀን በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በአዶላ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ና ታዛቢዎች በተገኙበት በአዶላ ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ አለመገኘት የጨረታውን መክፈት እያስተጓጉለውም፡፡

7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን እቃ በታዘዘው ጥራት እና ብዛት መሰረት አዶላ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ያስረክባል፡፡

8. ጨረታው የሚካሄደው በአፋን ኦሮሞ ቛንቛ ይሆናል፡፡

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

10. ስለ ቀድሞ መልካም አፈጻጸም መረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ያቀረበ ተወዳዳሪ ዋጋና ቴክኒካል ከሌላው ተወዳዳሪ ጋር እኩል ቢሆን ቅድሚያ ላቀረበው ይሰጣል፡፡

11. ጨረታው የሚካሄደው በአፋን ኦሮሞ ቛንቛ ይሆናል፡፡

12 መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 335 0773

የአዶላ ወዩ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህን ማስታወቂያ ከታተመበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች
  • Bid opening: 2026-09-25 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው 15 የስራ ቀናቶች ከተጠናቀቀ በኋላ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adola Weyu Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 2% ያላነሰ ብር 50.000.00 (ሀምሳ ሺ ብር)
  • Bid document price: 900.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T11:06:59.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders