Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና የተለያዩ የሞተር ሳይክሎችንና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል
More tags
Description
የዕቃ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2019
የኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ።
- የጽህፈት መሳሪያዎችን፣
- የጽዳት እቃዎችን፣
- የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎችንና ኤሌክትሮንክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና የተለያዩ የሞተር ሳይክሎችንና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።
የመወዳደሪያ መስፈርት
1. በንግድ (በስራ) ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የስራ ፍቃድ ያላቸውና የገቢዎች ቢሮ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
2. እቃ አቅራቢዎች በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የታደሰ ሕጋዊ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ብር 10,000/ አስር ሺህ/ ማስያዝ የሚችል፣
4. እቃ አቅራቢው የሚገዛውን እቃ በራሱ የማጓጓዣ ወጪ መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችል፣
5. የሚቀርበው ቋሚ የቢሮ ዕቃ ያልተገጣጠሙ ከሆኑ በራሱ ወጪ ማስገጠም የሚችል፣
6. የሚወዳደሩባቸውን የዕቃ አይነት ማለትም ለአላቂ የጽህፈት መሳሪያ፤ አላቂ የጽዳት እቃዎችና ብትን የደንብ ልብስና ሸሚዞች ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ
1. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርባቸው የምስክር ወረቀቶች በጉልህ የሚታዩና የሚነበቡ መሆን አለባቸው። የቀረበው ማስረጃ ግልጽነት የሌለውና የማይነበብ ከሆነ ዋጋ አይኖረውም።
2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት በመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድና የጨረታውን መመሪያ ስለመቀበላቸው የሚያረጋግጥ በጨረታ ሰነዱና የጨረታ መመሪያ ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው ስልጣን ባለው አካል በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በመለየት በፖስታ (Envelope) በማድረግና በሰም በማሸግ በአንድ ፖስታ ውስጥ አድርጎ ማቅረብና አስመዝግቦ በጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል። በቀረበው የጨረታ መመሪያና የጨረታ ሰነዶች ላይ ካልተፈረመና የድርጅቱ ማህተም ካልተደረገበት የጨረታ ሰነድ አካል የሆነውን የተጫራቾች መመሪያ እንዳልተቀበሉ በመቁጠር ያቀረቡት የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ውጪ ወይም ውድቅ ይሆናል።
3. ተጫራቾች በጨረታው መሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ጊዜ ጀምሮ ያስያዙት CPO ወይም ጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ግን ውል ከተፈራረሙና የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ካስያዙ በኋላ ተመላሽ ይሆናል።
4. ማንኛውም ተጫራች የተጠቀሰውን መስፈርት ያላሟላ ሰነድና ከላይ የተቀመጠውን እቃ ሳምፕል (ናሙና) ያላቀረበ እንደሆነ ከጨረታው ውጭ ይሆናል።
5. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል የቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመቅረብ የአንድ ጥቅል (lot) የጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡15 ኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ሂደት ክፍል የቢሮ ቁጥር 03 ጨረታው ይከፈታል።
8. 16ኛው ቀን ከሥራ ቀን ውጪ ቅዳሜ ወይም እሁድ ቀን ላይ የሚውል ከሆነ ሰኞ ዕለት የሚከፈት ይሆናል።
9. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. በሞተር ሳይክል እና በኤሌክትሮኒክስ ጥገና ላይ የሚሳተፉት ተጫራቾች በሞተር ሳይክል ጥገና እና በኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና የሥራ ፈቃድና ለሙያው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል።
11. ለሞተር ሳይክል ጥገና ወይም እድሳት እንዲሁም ለእቃ ግዥው ተጨማሪ ማብራሪያ ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ያገኛሉ።
አድራሻ
- ጅማ መንገድ ከአዲስ አበባ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ተጂ ከተማ ኢሉ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ያገኙናል።
- ለበለጠ መረጃ፦ የስልክ ቁጥር 0922177831, 0913165939, 0113390241
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-25 10:15
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15
- Region: Oromia
- Publishing entity: ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T11:06:59.000Z
- Source: 2merkato