Kitchen Equipment

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ/ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ

 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለወ/ሪት ጽዮን ጌታቸው የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች በዱቤ ግዥና ኪራይ ያስተላለፈ ቢሆንም ደንበኛዋ በውሉ መሠረት የኪራይ ከፍያ ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የዳቦ መጋገሪያ ማሽኖችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ.

የንብረቱ ዝርዝር

 

ብዛት  በቁጥር

 

የጨረታው መነሻ ዋጋ

 

የንብረቱ ሁኔታ

 

ጨረታው ሁኔታ

 

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

Baking Rotary Oven with Burner

  • Brand: PORLANMAZ, Model: PMDF200, Origin: Turkey

1

10,370,520.53

 

አዲስ

ድርድር  ጨረታ

መስከረም 27 ቀን 2019  ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እሰከ 6:00 ሰዓት

 


 

2

Mixer

  • Brand: PORLANMAZ, Model: PMSP120, Origin: Turkey

1

3

Dough Divider

  • Brand: PORLANMAZ, Origin: Turkey

1

4

Dough Moulder Machine

  • Brand: PORLANMAZ, Model: PMD350:Origin: Turkey

1

5

Proofer with Steam Generator

  • Brand: PORLANMAZ, Model: PMDF204, Origin: Turkey

1

Steamer

  • Model: PMCU10, Origin: Turkey

 

6

Trolley with 14trays

  • Brand: PORLANMAZ
  • Number of pans per trolley – 16
  •  material-stainless steel

4

7

Bread Slicer

  • Brand: PORLANMAZ, Model: PMBS500, Origin: Turkey

1

 

Sound Proof Generator

  • Brand: AKSA, Model: AP33, Rated power: 33KVA

1

የደርድር ጨረታ መመሪያ

  1. በድርድር ጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስምና አድራሻውን በመጥቀስ፣ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ፣ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር 2,074,104.11/ሁለት ሚሊዮን ሰባ አራት ሺ አንድ መቶ አራት ብር ከ11/100 ሳንቲም/ የያዘ በኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) እና የሚገዛበትን ዋጋ የሚገልጽ ማመልከቻ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢ/ት ልማት ባንከ ሀዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም.ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማመልከቻውን ማስገባት ይችላል፡፡
  2. ንብረቱ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ፣ መናኸሪያ ክ/ከተማ፣ ጉዊ ቀበሌ ባንኩ ከሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅ አ/ማ በተከራየው መጋዘን ውስጥ ነው፡፡
  3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ፈቃዱን ካላገኘ ግን የቀረጥ ክፍያው በገዥው ይፈጸማል፡፡
  4. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ/ በጥሬ ገንዘብ/ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች፣ የንብረቱ የሸያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል::
  5. የድርድር ጨረታው አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ የድርድር ጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል::
  6. ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል::
  7. የድርድር ጨረታው አሸናፊ፣ አሸናፊ ሆኖ አስፈላጊውን ሂደት ካጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ንብረቱን ለማስተዳደር የሚወጡ ወጪዎችን ማለትም የመጠለያ ኪራይ፣ የጥበቃ ክፍያ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት::
  8. የካፒታል ዕቃው ካለበት መጋዘን ወደሚፈልግበት ቦታ ማጓጓዣወጪ፣የጉዞኢንሹራንስ፣ መትከያ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው/ተከራይ ይሸፍናል::
  9. የድርድር ጨረታው ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በኢ/ት ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ቢሮ ውስጥ ይደረጋል፡፡
  10.  ስለንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል::
  11.  ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ሎን ዎርክአውት ዲቭዥን ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል::
  12. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በድርድሩ አይገደድም፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-07 10:00
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: (20%) ብር 2,074,104.11/ሁለት ሚሊዮን ሰባ አራት ሺ አንድ መቶ አራት ብር ከ11/100 ሳንቲም/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T11:13:58.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders