Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአምቦ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስልጠና የተለያዩ ለኢንዱስተሪያልስ፣ ለኤሌክትሮኒክስ፣ ለአውቶሞቲቭ፣ ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለጋርመንት ቴከኖሎጂ፣ ለኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ፣ ለዉድ ወርክ ቴክኖሎጂ እና ለአምቦ ዩኒት ፐሮዳክሽን የገቢ ምንጭ ለማምረቻ የሚያገለግሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን እና በተጨማሪም የስቴሽንሪ እና የፅዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 01/2019

የአምቦ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስልጠና የተለያዩ ለኢንዱስተሪያልስ ለኤሌክትሮኒስ ለአውቶሞቲቭ ለማኑፋክቸሪንግ ለጋርመንት ቴከኖሎጂ ለኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ለዉድ ወርክ ቴክኖሎጂ እና ለአምቦ ዩኒት ፐሮዳክሽን የገቢ ምንጭ ለማምረቻ የሚያገለግሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን እና በተጨማሪም የስቴሽንሪ እና የፅዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬትን ማቅረብ የምችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች የገንዘብ ሚኒስተር የታደሰ የምዝገባ ወረቀት በግልጽ የሚነበብና በበጀት ዓመቱ የታደሰ ማቅረብ የሚችል።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደርያ ሰነድ ኮሌጁ ባዘጋጀው እስፔስፊኬሽን መሰረት ብቻ መሆን አለበት፡፡

4. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

5. የመጫረቻ ሰነዱን እያንዳንዱን ሰነድ አምቦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በማቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400(አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

6. ጨረታው ከተፈተ በኋላ ተጫራች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም። እንዲሁም ከተጠየቀው እስፔስፊኬሽን ውጪ እቃ ማቅረብ ኣይፈቅድም፡፡

7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ የዋጋውን 10% በባንክ በተመሰከረለት የጨረታ ማስረከቢያ ሲ.ፒ.ኦ ብር 45,000(አርባ አምስት ሺህ ብር) ብቻ ማስያዝ ኣለባቸው፡፡ ጥሬ ገንዘብ ተቀባይነት የለውም።

8. ፋይናንሻልና ቴክኒካል ፕሮፖዛል ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ሰነዱን በመግባት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን 10ኛው(በአስረኛው) ቀን ከጠዋቱ በ8:00 ተዘግቶ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም የመንግስት ግዢ ኢንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡

10. አሸናፊው የዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝና ውል መፈረም አለበት

11. ተጫራቾች ማናቸውንም ያሸንፉባቸውን እቃዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ አምቦ በሚገኘው ለኮሌጁ ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።

12. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡

13. ዋጋ የሚሞላው ኮሌጁ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ምንም ማሻሻያ ሳይደረግበት ማቅረብ አለበት፡፡

14. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

ለተጨማሪ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር፡ 0112 362 196 ወይም 0909 117 533 / 0911 892 945 በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የአምቦ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው (በአስረኛው) ቀን ከጠዋቱ በ8:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-18 14:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው (በአስረኛው) ቀን ከጠዋቱ በ8:30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Ambo Polytechnic College
  • Bid bond: 45,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T11:45:25.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders