Building Construction

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁመራ አየር ማረፊያ የፌዴራል ፖሊስ መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ 4 (አራት) የጥበቃ ማማዎች ግንባታ እና የፌዴራል ፖሊስ መኖሪያ ቤት ጥገና (Construction of Federal Police Residence, 4 (Four) Blocks of Watchtowers and Maintenance of Existing Federal Police Residence Building at Humera Reg

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- SSNT-T639

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁመራ አየር ማረፊያ የፌዴራል ፖሊስ መኖሪያ ቤት ግንባታ፣ 4 (አራት) የጥበቃ ማማዎች ግንባታ እና የፌዴራል ፖሊስ መኖሪያ ቤት ጥገና (Construction of Federal Police Residence, 4 (Four) Blocks of Watchtowers and Maintenance of Existing Federal Police Residence Building at Humera Regional Airport) ብቁ የሆኑ ደረጃ-4 እና ከዚያ በላይ የመንገድ/ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC-4 እና ከዚያ በላይ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁለት (2) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ ተጫራቾች የእያንዳንዱ ፕሮጀክት አፈጻጸም ከ80% በታች ከሆነ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277( E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T639 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል ዓርብ, መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ -

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4918

ኢ-ሜይል: [email protected]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-10-09
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-10-09 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T11:49:00.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders