Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በወረዳ 04 ስር የሚገኘው ጀሞ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ጀሞ 01/2019

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት በወረዳ 04 ስር የሚገኘው ጀሞ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ ማሰራት ይፈልጋል::

የሎት ዓይነቶች

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን

ሎት አንድ

የደንብ ልብስ

24000

ሎት ሁለት

የፅዳት እቃዎች

25000

ሎት ሶስት

ቋሚ እቃዎች

25500

ሎት አራት

የጽህፈት አላቂ እቃዎች

22500

ሎት አምስት

የቢሮ አላቂ እቃዎች

15000

ሎት ስድስት

አጋዥ መፅሃፍት

3500

ሎት ሰባት

የላብራቶሪ እቃዎች

3000

ሎት ስምንት

ማሽነሪ ጥገና

3000

ሎት ዘጠኝ

የህትመት ስራ

3500

ሎት አስር

የጥገና ስራ የክፍል በር በአዲስ መስራት፤ የመስታወት ጥገና ጅብሰም ቦርድ ስራ

11000

ሎት አስራ አንድ

የሬዲዮ ትምህርት መስመር ጥገና

5000

በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

1. የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ::

2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስና ግዢ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ::

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በሰንጠረዡ ስር በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ( CPO ) ኦሪጅናል እና ኮፒ ብሎ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11 የስራ ቀናት 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ (specification) ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም፡፡

5. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው በጨረታ መሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች በትምህርት ቤቱ ስም የተፃፈ ደብዳቤ እና የጨረታውን ቁጥር ጠቅሰው በመፃፍ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ( CPO ) ያስይዛሉ፡፡

7. ተጫራቾች ሎት 1 ፤ ሎት 2 ፤ ሎት 4 ፤ ሎት 5 ፤ ሎት 7 ፤ ሎት 9 የተመረጡ እቃዎችን ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በተጨማሪም ሎት 3 ፤ ቋሚ እቃዎች በፎቶ በተደገፈ ማስረጃ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ሎት 10 የጥገና ስራ ደረጃ 7 እና ደረጃ 8 የሆኑ ተቋራጮች ብቻ መወዳደር ይችላሉ::

9. ሎት 10 የጥገና ስራ ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝቶ መጫረት እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማሰራት እና አሸናፊም ሲሆን የውል ማስከበሪያ የማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡

10. ጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በትምህርት ቤቱ ላይብረሪ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን ካላንደር የሚዘጋው ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡

11. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻችን፡- ከአየር ጤና ወደ ዓለም ባንክ በሚወስደው መንገድ ከወረዳ 04 ትንሽ ከፍ ብሎ

ስልክ ፡- 0118-35-30-56

የጀሞ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-19 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranyo Sub City, Jemo Pre-Primary and Junior High School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T11:58:42.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders