Equipment and Accessories

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ Supply & fix IP TV and digital Signage ሥራ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር DCE/SF/119/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፈደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በዝርዝር የተጠቀሰውን Supply & fix IP TV and digital Signage ሥራ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

/

 

የዕቃውን አይነት

 

የፕሮጀክት ስም

 

የጨረታ ቁጥር

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

 

 

Supply & fix IP TV and digital Signage

ፈደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን

 

DCE/ SF/119/2026

 

መስከረም 13/2019 . 4.00 ሰዓት

መስከረም 13/2019 . 4.15 ሰዓት

200,000.00

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ...ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

 3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲሱ ቢሮ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ ውስጥ

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የቀጥታ ስልክ ቁጥር 091117 751/0913297297
E-mail አድራሻ [email protected] 
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com 
ቃሊቲ ቶታል ማድያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-23 10:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 09, 2026)
  • Posted at: 2026-09-09T08:19:52.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders