Building Construction
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግለፅ ጨረታ ኮኖር ወንዝ ድልድይ (konor river bridge construction) መገንባት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አሽጨ/0016ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም
1.በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግለፅ ጨረታ ኮኖር ወንዝ ድልድይ (konor river bridge construction) መገንባት ይፈልጋል፡፡
2.በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር/supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3.ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
4.ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00 -6፡00፣ ከሰዓት በኃላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00 6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተጠቀሰው ነው፡-
5.1. አሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ፡፡
ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85/0986 862 766/ 0940 209 464
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
6. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች አንድ ላይ የጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በሲ.ፒ.ኦ. ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7.የድልድይ ግንባታ ደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ኦሞ ዞን ሳለማጎ ወረዳ ፋብሪካ የሚገኝበት ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው፡፡
8.ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡
9.የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡
10.ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ Tel- 0940 209 464 ኃይል ውሃ
አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ
Tel: 09-91-14-94-85 /0986 86 2766
አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ ስኳር አንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-09-23
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል፡፡
- Bid opening: 2026-09-24 12:00
- Bid opening (note): የጨረታውን መክፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Omo Kuraz No-2 Sugar Factory
- Bid bond: 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 09, 2026)
- Posted at: 2026-09-09T08:35:02.000Z
- Source: 2merkato