Sport Materials and Equipment

የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል በግልፅ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል በግልፅ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በመሆኑም

1ኛ አንደኛ ደረጃ የባለሞያ የስፖርት ትጥቅ

2ኛ የሬስቶራንት የምግብ እሽግ መጠጥ እና ትኩስ መጠጥ

3ኛ የደንብ ልብስ

4ኛ 2ኛ ደረጃ የአሰልጣኝ የስፖርት ትጥቅ

5ኛ ልዩ ልዩ ኳሶች

6ኛ ማልያና ቁምጣ

7ኛ የፅህፈት መሳሪያ

8ኛ አላቂ እቃ ማለትም

ሶፍት የገላ ሳሙና የልብስ ሳሙና የእቃ ሳሙና ፈሳሽ ስፖንጅ የእቃ ማጠቢያ ሽቦ አጃክስ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች

1. ለመጫረት የምትፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች በስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ሕጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. በመንግስት የግዢ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል /TIN/ ያላቸውና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. የንግድ ስራ መስክ የሚገልፅ በጀርባዉ ኮፒ ተደርጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የዘመኑን ግብር የከፈሉበትና ቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል፡

5. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር ይፈለጋል ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡

6. ተጫራቾች በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን ተወዳድረው ካሸነፉና ከተዋወሉ በኋላ ያሸነፉበትን እቃ ለማቅረብ ፈቃደኛ ካልሆነ በውሉ መሰረት በሕግ ይጠየቃሉ፡፡

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ሲሞሉ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣

8. የተጫራቾች ሙሉ ስም ፊርማ ማህተም ያረፈበት አድራሻ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥር አና ስልክ ቁጥራቸውን መግለዕ መሙላት ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከማዕከሉ አስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ ቀርቦ የማይመለስ 200 ብር መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ የሚያበቃና ሳጥኑም ታሽጎ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል የስራ ቀን ካልሆነ ግን በማግስቱ በስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. ተጫራቾች ጨረታውን በሚከፈትበት እለት ድርጅቱን የሚገልፅ ሕጋዊ መታወቂያ እና ውክልና የሚገልፅ ደብዳቤ በመያዝ ጨረታው ሲከፈት መከታተል ይቻላል።

12.ተጫራቾች የገዙት የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

13, ጨረታው በግልፅ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም መረጃ ዶክመንት ማቅረብ አይቻልም፡፡

14. አሸናፊዎች ክፍያ የሚከፈለው የተጠየቀው እቃ በተጠየቀውና ባሸነፈው መሰረት ሙሉ በሙሉ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ተደርጎ ሞዴል 19 ከተቆረጠ በኋላ ነው።

15. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ የትራንስፖርት አገልግሎት መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡

16. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ ሲፒኦ /CPO/ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

17. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ሳንጥል ማቅረብ አለባቸው

18. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የጃንሜዳ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማእከል


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር የስራ/ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-21 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር የስራ/ ቀናት ቆይቶ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 400 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Janmeda Sport Education Training Center
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 09, 2026)
  • Posted at: 2026-09-09T09:18:13.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders