Cleaning and Janitorial Equipment and Service
አበባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ. በጎተራ የሚገኘውን ዋና መሥሪያ ቤትና ጋራዥ እንዲሁም በጉርድሾላ የሚገኘውን ጋራዥ የጽዳት እና የጥበቃ አገልግሎት ለሁለት ዓመት በውጭ ድርጅት ለማሰራት በጨረታ ብቃት ያላቸውን የጽዳትና የጥበቃ አገልግሎት ድርጅቶች ይጋብዛል
Description
አበባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ.
የጽዳት እና የጥበቃ አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
አበባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ. በጎተራ የሚገኘውን ዋና መሥሪያ ቤትና ጋራዥ እንዲሁም በጉርድሾላ የሚገኘውን ጋራዥ የጽዳት እና የጥበቃ አገልግሎት ለሁለት ዓመት በውጭ ድርጅት ለማሰራት በጨረታ ብቃት ያላቸውን የጽዳትና የጥበቃ አገልግሎት ድርጅቶች ይጋብዛል።
የአገልግሎቱ ወሰን
1. የጥበቃ አገልግሎት
Ø ጎተራ ዋና መሥሪያ ቤትና ጋራዥ፡ 9 የጥበቃ ሠራተኞች (8 ወንድ፣ ከነዚህ 1 ሱፐርቫይዘር፣ እና 1 ሴት የቀን ቁጥጥር/ፍተሻ)።
Ø ጉርድሾላ ጋራዥ፡ 6 ወንድ የጥበቃ ሠራተኞች፣ ከነዚህ 1 ሱፐርቫይዘር።
Ø የጥበቃ አገልግሎቱ 24 ሰዓት በሶስት ፈረቃዎች ይሰጣል።
2. የጽዳት አገልግሎት
Ø በጎተራ ዋና መሥሪያ ቤት ብቻ 4 ሴት የጽዳት ሠራተኞች በአንድ ፈረቃ የሚሰሩ ይሆናሉ።
የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ
ፍላጎት ያላቸውና በዘርፉ ሕጋዊ ምዝገባ ያላቸው ድርጅቶች የሕጋዊነት፣ የቴክኒክ ብቃት፣ የተመሳሳይ ሥራ ልምድ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ከዋጋ ማቅረቢያቸው ጋር በማቅረብ መሳተፍ ይችላሉ።
የጨረታ ዋስትና፡ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በCPO ወይም በባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) መሆን አለበት።
የጨረታ ጊዜ፡ ጨረታው ከመስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም. (09/09/2026) ጀምሮ ለ15 ቀናት ክፍት ይሆናል። የመዝጊያ ቀን፡ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. (23/09/2026)።
የጨረታ ሰነዱንና ተጨማሪ መረጃዎችን ከአበባ ትራንስፖርት ዋና መሥሪያ ቤት ጎተራ፣ ከፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ጽ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 200 ከፍለው ማግኘት ይቻላሉ።
አበባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ.
ሰው ሀብት እና ጠቅላላ አገልግሎት መምርያ
ስልክ፡ +251965108202
Tender details
- Deadline: 2026-09-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-25 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ABEBA TRANSPORT PRIVATE LIMITED COMPANY
- Buyer address: መገናኛ አካባቢ ከእግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን 400 ሜትር ገባ ብሎ ሜጋ ማተሚያ ፊት ለፊት
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: 2merkato.com (Sep 10, 2026)
- Posted at: 2026-09-10T12:10:02.000Z
- Source: 2merkato