Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ LP/OT/003/OKSF1&3/2019

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት እቃዎች እና የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ስነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ ፣የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራጮች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ጉሩፕ

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

ግዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)

አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ፣

ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ

በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሱ

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ

ሕ-B ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ፣:

የስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251963442882+251913544731/251-916170834

አዲስ አበባ

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የፋብሪካ ኬሚካሎች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 14/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 14/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

5. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።

6. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 90 ቀናት ነው።

ፋብርካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-24 10:10
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T07:53:31.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders