Cleaning and Janitorial Equipment and Service

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል የተለያዩ የዕቃና አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የዕቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

የሎት ዓይነት

  • ሎት-1 የፅህፈት መሳሪያና ተዛማጅ እቃዎች
  • ሉት-2 የፅዳትና ተዛማጅ ዕቃዎች
  • ሎት-3 የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ተዛማጅ ዕቃዎች
  • ሎት-4 የኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች
  • ሎት-5 የህንፃ መሣሪያዎች ዕቃዎች
  • ሎት-6 የተለያዩ የግብርናና የደን ልማት ግብዓት
  • ሎት-7 የተለያዩ የቧንቧ ዕቃዎች
  • ሉት-8 የቋሚ ዕቃዎች
  • ሎት-9 የህትመት ሥራዎች
  • ሎት-10 የደንብ ልብስ
  • ሎት-11 የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት-12 የመኪና ዕቃዎች
  • ሎት-13 ውሃ
  • ሎት-14 የመስተንግዶ ጥሬ ዕቃዎች
  • ሎት-15 የህፃናት መፅሐፍት

ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ባቀረበው ጨረታ ላይ ለመካፈል የዘመኑ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታደሰ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ እና በፌደራል ግዥ ንብረት አስተዳደር ድረ-ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

1. የጨረታ ማስከበሪያ ሎት-1፣ ሎት-2፣ ሎት-5፣ ሎት-6፣ ሎት-7፣ ሎት-9፣ ሎት-10፣ ሎት-11፤ ሎት-12፣ ሎት 13፤ ሎት-14 እና ሎት-15 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ እንዲሁም ሎት-3፣ ሎት-4 እና ሎት-8 ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተደራጅተው ለሚጫረቱ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያው እና የውል ማስከበሪያው ከአደራጀው አካል የዋስትና ደብዳቤ በዘርፉ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ በየሎቱ የተጠመሩትን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾችጨረታው ከተከፈተበኋላቀደምሲል ባቀረቡትየመወዳደሪያሃሳብለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም። በተጨማሪም ናሙና ማምጣት የሚቻለው የመጀመሪያ የሰነድ ግምገማ ተጣርቶ ውጤት ከታወቀ በኋላ የሚቀርብ ይሆናል።

4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ሲያስገቡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መሆን ይኖርበታል። ስሌት ሲሰላ ስህተት ቢኖረው መ/ቤቱ የሚወስደው ነጠላ ዋጋውን ይሆናል። እንዲሁም የጨረታ ዋጋ በሚያስገቡበት ወቅት ማዕከሉ በሸጠው ሰነድ ብቻ መሆን አለበት በተጨማሪም ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ እና ተጨማሪ ፅሑፎች ማስገባት በጨረታው ላይ ተቀባይነት የለውም።

5. ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስገቡት ዋጋ ቆይታ ጊዜ 60 ቀን ሲሆን፣ ከ6ዐ ቀን ያነሰ ጊዜ ማስገባት ከውድድር ውጭ ያደርጋል።

6. ከላይ የተጠቀሱትን ለጨረታ የሚያስፈልጉ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) እና (ቴክኒካል) ሰነዶች ኦርጂናል ለብቻ በአንድ ፖስታ እና ቴክኒካል ሰነዶች ኮፒ ለብቻ በአንድ ፖስታ ተደርጎ በእያንዳዳቸው የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ ለየብቻ በማሽግ በአጠቃላይ ሁለት ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን (ፋይናንሻል) ሰነዶች ኦርጂናል ለብቻ በአንድ ፖስታ እና የዋጋ ማቅረቢያውን (ፋይናንሻል) ሰነዶች ኮፒ ለብቻ በአንድ ፖስታ በማድረግ በእያንዳዳቸው የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ በማሸግ ሁለት ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የጨረታ ሰነዶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 /አሥራ/ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 10% {አሥር በመቶ (CPO) በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።

10. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

11. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 154 7226 ደውለው ያነጋግሩ

ህንፃ ቁጥር 2 1ኛ ፎቅ ላይ

አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፅዮን ሆቴል 800 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ያለው ማዕከል ፊት ለፊት

የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-23 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Botanic Garden
  • Buyer address: ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በፅዮን ሆቴል 800 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ስሙ አጣሪ ሰፈር ባለው የማዕከሉ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T08:06:24.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders