Food and Beverage

በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ ልዩ ልዩ የምግብ ግብዓቶችና የበሰሉ ምግቦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለካምፓሱ ሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የምግብ ግብዓቶችና የበሰሉ ምግቦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. ለተጠየቁት ምግቦች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ፣ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላችሁ ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚትችሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በካምፓሱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመቅረብ ሰነዱን 500.00 /አምስት መቶ/ ብር ባንክ ገቢ በመድረግ በግዥ መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ጠዋት 3:00 ሰዓት ማቅረብ እና ሳጥን መስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካምፓሱ አዳራሽ ይከፈታል።

4. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የተወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ(C.PO.) ለእህል እና ፍራፍሬ ብር 100,000.00/መቶ ሺህ/ ፡ስጋ፡ዳቦ፡ ማገዶ ብር 30,000.00/ ሠላሳ ሺህ/ በካምፓሱ ስም በመስያዝ ማቅረብ ይኖርበታል።

5. አሸናፊው ተጫራች አስተማማኝ የሆነ የምግብ ክምችት ያለውና ምግቦቹንና የምግብ ግብዓቶችን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ በሚገኘው በካምፓሱ ግቢ ድረስ አምጥቶ ካምፓሱ በምሰጠው ፕሮግራም መሰረት ማስረከብ ይኖርበታል።

6. ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁፕር 0930107417/0911742980/ ይጠይቁ።
በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አሰላ ካምፓስ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-29
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-29 09:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Oromia State University
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T08:19:20.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders