Veterinary Equipment and Supplies

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች/ሰፔር ፓርት፣ የተለያዩ የእንሰሳት መድሃኒቶች በመደበኛ በጀት እና በሪቦልቢንግ ፈንድ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨ/መለያ የቁ/ግንአስ_069/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡-

  • ሎት 01 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች/ሰፔር ፓርተ፣
  • ሎት 02 የተለያዩ የእንሰሳት መድሃኒቶች በመደበኛ በጀት እና በሪቦልቢንግ ፈንድ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነበር/የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸዉን የገቢ ክሊራንሰ እና የቫት ሰርተፍኬት ያላቸውና ለእንሰሳት መድሃኒቱ ፣የሚሞሉት ዋጋ ከ500,000 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅርብ አለባቸው።

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢት.ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፍል ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች (ፕርፎርማንስ ቦንድ) በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በሆኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና Unconditional Bank Guarantee/ ለመኪና እቃዎች በቁርጥ 70,000; /ሰባ ሽህ ብር እና ለእንሰሳት መድሃኒቶች በቁርጥ 10,000 /አስር ሺህ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ማስያዝ ይኖርበታል።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን፣ ሎት 01 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች/ሰፔር ፓርት 02 የእንሰሳት መድሃኒቶች ጧት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

5. የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ስዓት ይተላለፋና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጃናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ስዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

8. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

9. ማንኛውም እቃ ጽ/ቤቱ በሚፈልገውና ባዘጋጀው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ስለማቅረቡ በሙከራና በባለሙያ አረጋግጦ የሚረከብ መሆኑ ይታወቅ።

10.ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች 033 336 01249 ወይም 09 11 57 91 38 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በ16ኛው ቀን ጧት 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-30 12:00
  • Bid opening (note): በ16ኛው ቀን ጧት 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Lasta Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T08:33:43.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders