Stationery
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳ ማሊማ ወረዳ ፍ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ መሳሪያዎችን፣ የንጽህና መሳሪያዎችን፣ አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳ ማሊማ ወረዳ ፍ/ቤት ለፍርድቤቱ የሚያስፈለገው፤ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ መሳሪያዎችን፤ የንጽህና መሳሪያዎችን፤ አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
1. እቃዎችን በጥራት ለማቀረብ የሚያስችል ህጋዊ በ2019ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
2. በገ/ኢ/ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ አካል በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
3. ተወዳዳሪዎቹ መንግስት ባወጣው ህግ መሠረት የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
4. የግብር ከፋይነትና የአመቱን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርብ፣
5. ተወዳዳሪው ከሙስናና ከማጭበርበር ተግባር የፀዳ ስለመሆኑና ሃገራዊና ክልላዊ ደንቦችን በማክበር ጨረታውን ካሸነፈ ውሉን ለማፈራረም የተዘጋጀ መሆን አለበት።
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተወዳዳሪ ማሻሻያ ወይም ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ መውጣት አይቻልም፤
7. ተወዳዳሪው የእቃ ናሙናና በሙሉ ወይም በከፊል ሲጠየቅ እስከ ወረዳው ፍ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል። ናሙና ማቅረብ የማይችሉ እቃዎች የአምራች ሀገር፤ የእቃው ስም፤ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበት ዘመን በመዘርዘር እንዲሁም የፎቶግራፋቸውን አልበም ማቅረብ አለበት። ለናሙና የቀረበው እቃ አስፈላጊው ግምገማ ከተከናወነ በኋላ ለባለቤቱ ይመለሳል።
8. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ 2000 /ሁለት ሺ ብር/ በጥሬ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ/ በመክፈል በወረዳው ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
10. የጨረታ ሰነዱን በአንድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በንግድ ድርጅቱ ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞናማህተም አርፎበት ማቅረብ አለበት።
11. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ወረዳው ፍ ቤት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
12. ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ጨረታውን ማሸነፉ ተገልጾለት እስከ 5 ቀናት ድረስ ቀርቦ የግዥውን ጠቅላላ 10% በገንዘብ በማስያዝ ውሉን መፈረም አለበት። ያስያዙት ብር ተመላሽ የሚሆነው እቃውን ሙሉ በሙሉ ካቀረቡ በኋላ ይሆናል።
13. ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣ ቀን አንስቶ እስከ 5 /አምስት/ ቀናት ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው ሰነድ ላይ መግለጫ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል።
14. ይህን ጨረታ ለማደናቀፍ የሚሞክር ተወዳዳሪ ከጨረታ ውጪ በመሆን ለወደፊትም መንግስት በሚያወጣው ጨረታ ላይ እንዳይካፈልና የጨረታው ማስከበሪያው የማይመለስለት ይሆናል።
15. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እስከ ወረዳ ፍ/ቤት የማቅረብ ግዴታ አለበት።
17. አድራሻችን ከአ/አበባ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ ላይ 60 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ሌመን ከተማ ይገኛል።
18. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር-011 363 0078፤ 011 363 0028፤ 09 27 83 46 45 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳ ማሊማ ወረዳ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-30 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Kersa Malima Woreda Court
- Bid bond: 2000 /ሁለት ሺ ብር/
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T08:46:15.000Z
- Source: 2merkato