Stationery

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን የተለያዩ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/GO01/2019

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን፡-

  • ምድብ አንድ፡ የቢሮ(የጽሕፈት) እቃዎች
  • ምድብ ሁለት፡ አላቂ የጽዳት እቃዎች
  • ምድብ ሶስት፡ የስራ ልብስ እና ጫማ
  • ምድብ አራት፡ የኮምፒውተር እቃዎች እና ተያያሽ እቃዎች
  • ምድብ አምስት፡ ሕትመት
  • ምድብ ስድስት፡ የተለያዩ የቢሮ ብረት ሼልፎች እና
  • ምድብ ሰባት፡ የኤሌክትሪክ እና የኢንተርኔት እቃዎች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የህዝብ መናፈሻ ጎን ዲቪዥን ጽ/ ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። የክፍያ ሁኔታ በኤሌክትሮኒክስ ማስተላለፍ።

2. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት በፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ሰርትፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

3. በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኤሌክትሮኒክ ትራንስፈር ለምድብ አንድ፣ሁለት እና ሶስት ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፣ ለምድብ አራት እና አምስት ለእያንዳዳቸው ብር 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)፣ ለምድብ ስድስት ብር 35,000.00 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር)፣ ለምድብ ሰባት ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል። ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።

4. አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈባቸው የዕቃ ዝርዝር የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል።

5. የሚገዙ እቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን 20% ሊጨምር ወይም 20% ሊቀንስ ይችላል።

6. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ 60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት። ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።

7. የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።

8. ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ 8፡30 5ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

9. ተጫራቾች ዲቪዥን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል። የሚቀርበውዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።

10. ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- +251 11 557 9036(1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል)

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና ፍሳሽ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-10-07 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Water and Sewerage Authority
  • Buyer address: ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ-08 ፣ የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T08:52:16.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders