Stationery

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገለግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ህትመቶች፣ የጽዳት እቃዎች ቋሚ የቢሮ ውስጥ ፈርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ኮምፒውተሮች የመሳሰሉትን/፣ ጄኔተሮች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የሥልጠና ዕቃዎች እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገለግሎት የሚውሉ

  • የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  • ህትመቶች፣
  • የጽዳት እቃዎች ቋሚ የቢሮ ውስጥ ፈርኒቸሮች፣
  • ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ኮምፒውተሮች የመሳሰሉትን/፣
  • ጄኔተሮች፣
  • የግንባታ ዕቃዎች፣
  • የሥልጠና ዕቃዎች እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመገዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1.ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. በገንዘብ ሚ/ር የዕቃ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያለው

4. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዕቃዎቹን እስፔስፊኬሽን የማይመለስ በር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአብቹና ኘኣ ወረዳ ፍ/ቤት በመምጣት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒውን በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 08 መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውሰጥ ማስገባት አለባቸው።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 /አሥር ሺህ/ በባንክ የተመሠከረ (CPO) ማቅረብ የሚችል።

7. ጨረታው የሚከፈተው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ7፡40 ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ7፡40 በወረዳ ፍ/ቤት ይከፈታል።

8. አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን አብቹና ኘኣ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ በመምጣት ማስገባት አለበት።

9. የተጠየቁትን ዕቃዎች ሠርዘው ወይም ደልዘው መጻፍ ክልክል ነው።

10. የዕቃውን ኮድ ወይም አይነት ለመቀየር ከፈለጉ ከታች ማሳሰቢያ ብለው በመፃፍ ይፈርሙበት።

11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታወን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝመብቱ የተጠበቀ ነው።

12. የተጠየቁት ዕቃዎች በሙሉ ደረጃቸውን የጠበቁና ኦርጂናል መሆን አለባቸው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 12 66 51 57/ 011 621 0053/24

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ፍ/ቤት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-29 13:40
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው የሥራ ቀን ሆኖ በዚሁ ቀን በ7፡40 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የአብቹና ኘኣ ወረዳ ፍ/ቤት
  • Bid bond: 10000 /አሥር ሺህ/
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T09:03:44.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders