Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ የሚገኘው ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግዥው መለያ ቁጥር፡- 001/2019 ዓ.ም የእቃ እና የአገልግሎት ግዥ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ የሚገኘው ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ማለትም
- ሎት 1 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃ፣
- ሎት 3 አላቂ የህትመት እቃዎች፣
- ሎት 4 አላቂ የህክምና እቃዎች፣
- ሎት 5 አላቂ የማስተማሪያ እቃዎች፣
- ሎት 6 አላቂ የዕዳት እቃዎች፣
- ሎት 7፣ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
- ሎት 8 ፣የማሽነሪ እቃዎች ጥገና፣
- ሎት 9 የጥገና እቃዎች፣
- ሎት 10 ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት 11 የመኪና የጭነት አገልግሎት፣
- ሎት 12 የተለያዩ መፅህፍት፣
- ሎት 13 የጉልበት ስራ አገልግሎት በመስኩ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በተሰማሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈለቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የገቢዎች ክሊራንስእና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፍቃድ የተመዘገበ የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረ/ በ ሲፒዮ (CPO) ለቆጣሪ /የመ/ደ/ት/ቤት ተብሎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 19400.00፣
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 2560.8 ፣
- ሎት 3 አላቂ ህትመት እቃዎችብር 3880.00፣
- ሎት 4 አላቂ የህክምና እቃዎች ብር 310.40 ፣
- ሎት 5 የማስተማርያ እቃዎች ብር 13968.00፣
- ሎት 6. አላቂ የፅዳት እቃዎች ብር 4512.00፣
- ሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 1241.60፣
- ሎት 8 የማሽነሪ እቃዎች ጥገና ብር 1152.00
- ሎት 9 የጥገና እቃዎች ብር 2986.86 ፣
- ሎት 10. ቋሚ እቃዎች ብር 12416.00
- ሎት 11 የመኪና የጭነት አገልግሎት ብር 1940.00
- ሎት 12.የተለያዩ መፅሀፍት ብር 310.40
- ሎት 13 የጉልበት ስራ አገልግሎት ብር 1940.00
3. ተጫራቾች በተወዳደሩባቸው ሎቶች ውስጥ ከሎት 8፣ ሎት 11 እና ሎት 13 የአገልግሎት ግዢ ከሆኑት በስተቀር በሌሎቹ እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የሚቀርቡት እቃዎች በተሰጠው ስፔሲፍኬሽን ካልቀረቡ እና ማንኛውም ስህተት ቢፈፀም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ይሆናል።
4. ት/ቤቱ የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን 20% በመጨመር ወይም 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ አለበት።
5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብቻ) በቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት የውስጥ ገቢ አካውንት ቁጥር 1000011720165 ስኬት ባንክ የባንክ አድቫይስ በመያዝ ት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያሠንጠረዥ ላይ ብቻ ቫትን ጨምሮ ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ዋጋውን ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መታየት አለበት፤ ስርዝ ድልዝ ያለው ተቀባይነት የለውም።
7. ተጫራቾች የቴክኒክ ፣ የፋይናንሻል ሰነድና ሲፒዮ (CPO) ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን ፣ ፊርማቸውን እና ማህተም አሟልተው በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው የታሸገ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ውሎ በዚሁ ቀን 11፡30 ተጠናቆ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
9. የዘገየ ተጫራችና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም።
11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ
አድራሻ - አ.አ ን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ሀና ማርያም ቀለበት ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 011-4-71-11-90/0114195277
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 11 የሚገኘው ቆጣሪ የመ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-23
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ውሎ በዚሁ ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-24 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kotari Elementary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T09:46:49.000Z
- Source: 2merkato