Building Construction

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ለወ/ወ/ ከተማ ልማት ጽ/ቤት የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ፣ የወ/ወ/ስራና ስልጠና ጽ/ቤት ለ01 ሰርቶ ማሳያ፣ ለ06 ሠቃ ሽምብራ እና ለ027 ጣዬ ቀበሌዎች ሙሉ ማቴሪያል ችሎ የሸድ ግንባታ እና የወ/ወ/ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የገበያ ማዕከል ሙሉ ማቴሪያል ችሎ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ

Description

ሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ለወ/ወ/ ከተማ ልማት ጽ/ቤት የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ፣ የወ/ወ/ስራና ስልጠና ጽ/ቤት ለ01 ሰርቶ ማሳያ ፣ ለ06 ሠቃ ሽምብራ እና ለ027 ጣዬ ቀበሌዎች ሙሉ ማቴሪያል ችሎ የሸድ ግንባታ እና የወ/ወ/ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የገበያ ማዕከል ሙሉ ማቴሪያል ችሎ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤታችን ይጋብዛል።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መሰፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. የዘመኑ የታደሰና ህጋዊ ፈቃድ ያለውና የንግድ ስራ ዘርፉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ነምበር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣

3. የግዡ መጠን ከ500,000/አምስት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው የንግድ ስራ ፍቃድ ኮድ መሰረት ንግድ ፈቃዳቸውን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 25ኛው ቀን 11፡30 ድረስ 500 ብር (መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ይዘው መቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ25 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ26ኛው ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚያው በ26 ኛው ቀን ጨረታው 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን ይከፈታል።

9. የጨረታው መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለጸላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አስር/10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለበት።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ለከተማ ልማት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000 (አንድ መቶ አምሳ ሽህ ብር) ፣ ለስራና ስልጠና 25,000 (ሃያ አምስት ሽህ ብር) እና ለንግድና ገበያ ልማት 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) ለማስያዝ ይኖርባቸዋል።

13. ማንኛውም ተጫራች ነጠላ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።

14. ውድድሩ በጥቅል ድምር (ሎት) መሆኑን እንዲያውቁትና የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት የሚጠበቅበዎት መሆኑን አይዘንጉ።

15. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 45 /አርባ አምስት ቀን መሆኑ ይታወቅ።

16 .ተጫራቾች ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሚያሟሉ መሆን አለባቸው

ወግዲ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ25 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ26ኛው ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-07 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ25 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ26ኛው ቀን እስከ ጧቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Wogedi Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
  • Posted at: 2026-09-12T09:59:29.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders