Stationery
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና መከካለኛ ደረጃ ት/ቤት የስራ ዘመን የፅህፈት መሳሪያ፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና መከካለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም
- የስራ ዘመን የፅህፍት መሳሪያ እና
- ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እና
- የደንብ ልብስ ስፌት ማለትም
ከሎት 1 እስከ ሎት 10 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በግልፅ ጨረታ ተሳታፊዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፕኦ (cpo) ማቅረብ አለባቸው።
- ሎት.1 (አንድ ) 1 የፅህፍት መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች/ ወጪ መደብ 6212 0.50/ ብር 10534.81
- ሎት.2. (ሁለት ) 2 /(የጽዳት ዕቃዎች/ 6218 0.5 0/0 ብር 9357.40
- ሎት 3.(ሶስት) /(የደንብ ልብስ ስፌት/ 6211 0.5 % ብር 8500
- ሎት 4.(አራት) /(ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ) 6243 0.5 % ብር 1000
- ሎት 5.(አምስት)/(የትምህርት ዕቃዎች) 6215 0.5 % ብር 2624.65
- ሎት 6.(ስድስት)/( የሕክምና እቃዎች) 6214 0.5 % ብር 194.62
- ሎት 7(ሰባት) |(ህትመት ) 6213 0.5 % ብር 1053.24
- ሎት 8.(ስምንት) ልዩ ልዩ እቃዎች 6419 0.5 % ብር ከ1150
- ሎት 9. (ዘጠኝ)የሕንፃና ተገጣጣሚዎች ቁሳቁስ ና እቃዎች 6244 0.5 % ብር 2430.62
- ሎት 10.(አስር) ቋሚ ዕቃዎች 6314 0.5 % ብር 7500
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር /supplierlist/ በኦላይን መመዝገባቸውን ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እናማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን አለባቸው።
- የእሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 ( አራት መቶ ብር) ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ አንደኛ ደረጃ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት አካውንት ቁጥር 1000190858627 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ ከተማ / ክ/ ከ/ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 (አስራ ስምንት) ሳይሻገር ድልድዩ ስር ይገኛል የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ክፍያና/ሂ አስተዳደር ቢሮ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) የስራ ቀናት ከጥዋቱ 2፡30–11፡30 ከምሳ ሰዓት ውጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ያለውን እቃዎች ሁሉ ናሙና ማሳየት እና የቋሚ እቃ ፎቶ ሳንፕል እንዲሁም እቃውን ቦታው ድረስ ማሳየት ግዴታ አለባቸው።
- አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም።
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና (ቴክኒካል) ፎቶኮፒውን ሰነዶችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል። በአስራ አንደኛው ቀን ምንም አይነት የጨረታ ሰነድ የማንቀበል ይሆናል።
- የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክቁጥር መኖር አለበት።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ የተመለከተውን ጊዜገደብውስጥ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን የእቃ ዋጋ 10% ገቢ አድርገው ውል መዋዋል አለባቸው።
- መስሪያቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም ስራውን የማሰራት መብቱ የተጠበቀነው፡፡ የሚሰራው ስራ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
- በጨረታ ሰነድ መመሪያ ላይ በተጫራቹ የሚሞላ ሁሉንም ሰነድ መሞላት አለበት ሳይሞላ ቢቀር ጨረታው ላይ ውድቅ ቢሆኑ መስሪያ ቤቱ ሐላፊነት አይወስድም።
- ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በደጋፊ የስራ ሂደቱ የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ጨረታው ውጤት በተገለፀ በ7ቀን (ሰባት) ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ግዥው ከአሸናፊው ጋር ውል ይፈጽማል።
- አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ቀናት ውስጥ እቃውን ማስገባት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ያሸነፉበትን ደንብ ልብስ ስፌት የልብስ መስፊያ ማሸኑን ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት መስራት አለበት ፡፡ ሲጨርስ ለግምጃ ቤት ማስረከብ አለበት።
- ተጫራቾች በሚያቀቡት የወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚቀርቡት የስራ አይነት ዋጋ ላይ ሰርዝ ድልዝ የሌለበት ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይገባል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የአነስተኛ እና ጥቃቅን ተጫራቾች አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ በማምጣት ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በድርጅቱ የተከፈተ የባንክ አካውንት ቁጥር የሚገልጽ የመረጃ በፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል።
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ / ክ/ ከ/ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 (አስራ ስምንት) ሳይሻገር ድልድዩ ስር ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 011-2-73-90-66 ወይም 011-2-79-11-29
በአዲስ ከተማ ክፍስከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-23 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 11, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T10:20:54.000Z
- Source: 2merkato