Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር የሚከተሉትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ |
|
1 |
1 |
አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች |
5,850 (0.5%) |
|
2 |
2 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች |
6,500(0.5%) |
|
3 |
3 |
ቋሚ የቢሮ እቃዎች |
9,500 (0.5%) |
|
4 |
4 |
የህትመት ውጤቶች |
3,030(0.5%) |
|
5 |
5 |
የደንብ ልብስ |
4,505 (0.5%) |
|
6 |
6 |
የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች |
22,150(0.5%) |
|
7 |
7 |
መሠረተ ልማት |
7,605(0.5%) |
|
8 |
8 |
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እድሳትና ጥገና አገልግሎት |
1,450 (0.5%) |
|
9 |
9 |
የመኪና ክራይ |
1,050(0.5%) |
ተጫራቾች
1. በዘርፉ ከተሰማሩበት ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ተገቢዎች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በድህረ ገፅ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው በኦላይን የሚረጋገጥ ይሆናል።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ቲን ነበር ማቅረብ የሚችሉ
4. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
5. ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 401 ድረስ በመምጣት ሙሉ የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ሰነድ ይወስዳሉ። እንዲሁም ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ማስከበሪያ ከተደራጁበት ወረዳ ደብዳቤ ማምጣት አለባቸው።
7. ጨረታው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
10. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ወጪ የመሥሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት።
11. ጤና ጣቢያው በጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተጠቀሰው መጠን 20% ድረስ የመጨመር እና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ነው።
13. ተጫራቾቹ የጨረታውን ማስከበሪያ ሲፒኦ በየሎቱ ለየብቻ ማሠራት አለባቸው።
14. ተጫራቾች ሲፒኦ ኮፒ እና ኦርጅናል ይዞ መምጣት አለባቸው።
15. ተጫራቾች መደበኛ የጨረታ ሰነዱ ላይ በየአንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተብ እና ፊርማ ካላደረጉ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
16. ተወካዮችውል ለመዋዋልና ለተለያየ አገልግሎት ሲመጡ የውክልና ደብዳቤ ይዘው መምጣት አለባቸው።
17. ጤና ጣቢያው ተጫራቾች ውል ተዋውለው ለሚያቀርቡት እቃ ላይ እስከ 6ወር ድረስ በተመሳሳይ ዋጋ 20 በመቶ ተጨማሪ ግዥ ማከናወን ይችላል።
18. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታው መርካቶ አሜሪካን ግቢ ኡራጎ ሕንፃ ጀርባ የመን ኮሚኒቲ ት/ቤት አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡- 0112 732 872 / 0112 273 2594 / 0112 732 584
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-24 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ginbot 20 Health Post
- Buyer address: አ/ከ/ክተማ ወረዳ 1 ግንቦት 20 ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታው አሜሪካን ግቢ ኢራጎ ሕንፃ ጅርባ የመን ኪሚቲ ት/ቤት አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T10:32:45.000Z
- Source: 2merkato