Cleaning and Janitorial Equipment and Service

መልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001

መልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

1.በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የታክስ ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና በዘመኑ ግብር መክፈላቸው ሕጋዊ ደረሰኝ ወይም የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ሎት

የአገልግሎት አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

የጽሕፈት መሣሪያዎች እና አላቂ የቢሮ እቃዎች

19,983

ሎት 2

የደንብ ልብስ

54,000

ሎት 3

የፅዳት እቃዎች

30,000

ሎት 4

የትምህርት እቃዎች

10,000

ሎት 5

ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች

10,000

ሎት 6

ለማሽነሪ ጥገና

44,000

2. ተጫራቾች ከዚህ በላይ በሰንጠረዥ በሚመለከተው መሰረት በሚወዳደሩበት ሎት ፊት ለፊት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (cpo) በመልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ ቤት ስም በማሠራት ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል።

3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመስስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በየሎቱ በመክፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 መልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ቤት ግዢ ክፍል በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱንም ሆነ የጨረታ ማስከበሪያ እንዲሁም የውል ማስከበሪያ በነጻ መስተናገድ የሚችሉ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ሁሉ የአምራችነት ድጋፍ ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል ማምጣት የሚችሉት ማህበራቶች ብቻ ናቸው።

4. ትምህርት ቤቱ ያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልቶ እና የድረጅቱን ሕጋዊ ማህተም አድረጎ ማቅረብ አለበት።

5. የጨረታ ሰነዱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በዓል ካልሆነ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ስዓት የሚከፈት ይሆናል።

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የጨረታ ሰነድ በኤንቬሎፕ በማሸግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በግልጽ ለይቶ በመጻፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ሲሆን ለአንድ እቃ ከአንድ በላይ ናሙና ማቅረብ አይቻልም።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ገዥ ፈፃሚው መልካ ዳንሰ ትምህርት ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. የዘገዩ ጨረታ እና በመክፈቻ ላይ ያልተነበበ እንዲሁም ግልጽ ያልሆነ ወይም የማይነበብ ጽሑፍ በጨረታ ተቀባይነት የለውም።

9. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን መሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍስ ከተማ ወረዳ 14 ከሰፈራ ዝቅ ብሎ ወይም ኃይሌ ማራቶን ፊት ለፊት ሰላም ገሮሰሪ ገባ ብሎ ሀና ፉሪ አዲሱ ኮንዶሚኒዬም አጠገብ

መልካ ዳንሴ የመ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በዓል ካልሆነ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Melka Dance Elementary School
  • Buyer address: ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በሰፈራ ገላን መሄጃ በስተቀኝ 400 ሜ ገባ ብሎ አዲሱ ኮንዶሚኒም አጠገብ ነው
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Sep 13, 2026)
  • Posted at: 2026-09-14T08:43:36.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders