House and Building Sale

አዲስ ባንክ አ.ማ. መጋዘን እና ኮንድሚኒየም ለንግድ የሚሆን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

አዲስ ባንክ አ.ማ

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

አዲስ ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመከቱትን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ጨረታው በሚከናወንበት ቦታ በመገኘት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

ተ.ቁ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

አጠቃላይ የቦታ ስፋት

የንብረቱ ዓይነት

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር

ጨረታው የሚከናውንበት ቀንና

ከተማ

/ከተማ

1

አዲስ አበባ

ቃሊቲ ወረዳ 07

1350 . (መጋዘን ያረፈበት 1120  .)

መጋዘን

62,230,629.58

 

መስከረም 19 ቀን 2019 .ቀኑ 800

2

አዲስ አባባ

አራዳ ባሻ ወልዴ ወረዳ09

37.47 .

 

ኮንድሚኒየም ለንግድ የሚሆን

5,042,381.69

 

መስከረም 19 ቀን 2019 .ከቀኑ 900

ማሳሰቢያ፡-

  1. ንብረቶቹን ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች መስከረም 14 እና 15 ቀን 2019 ዓ.ም በስራ ስዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0115570319።
  2. የጨረታው ማስከበሪያ የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም 25 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ /ሲ.ፒ.ኦ በጨረታው ዕለት ይዞ በመምጣት መወዳደር ይቻላል።
  3. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ጨረታውን ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የክፍያ ሰነድ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  4.  ጨረታው መስከረም 19 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ ባንክ ግዥና ፋስሊቲ አስተዳደር መምሪያ ራኑ ሃ/የተ/የግ/ማ ህንጻ ከዝቋላ ኮምፕሌክስ ጎን በሚገኘው ስድስተኛ ፎቅ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከናወናል።
  5. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዘዋወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
  6. የጨረታው አሸናፊ ለመንግስት የሚከፈለውን አስፈላጊ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
  7. ለበለጠ ማብራሪያ አዲስ ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት በስልክ ቁጥር 0115 570319 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
  8. ባንኩ ንብረቱን ለመሸጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዲስ ባንክ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-29
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-29 15:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 13, 2026)
  • Posted at: 2026-09-14T11:24:08.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders