Textile, Garment and Leather

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል የደንብ ልብስ ግዥ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ፣ አላቂ የህክምና አቅርቦቶች፣ ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የእቃ ግዥ ጨረታ፤ጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/ቁ/01/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2019 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡-

  • ሎት 1፡- የደንብ ልብስ ግዥ፣
  • ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 3፡- አላቂ የህከምና አቅርቦቶች
  • ሎት 4፡- ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃዱን ያደሰ፤

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤ በeGP ምዝገባ የተመዘገበ፤

3. የአቅራቢነት ማስረጃ ያለው፤

4. ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ ማስከበሪያ

  • ሎት 1፡- የደንብ ልብስ ግዥ 250,000.00 ብር
  • ሎት 2፡- አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ 100000.00 ብር
  • ሎት 3፡- አላቂ የህክምና አቅርቦቶች 100000.00 ብር
  • ሎት 4፡- ሌሎች አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች ግዥ 350000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO)፣ ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

6.ተጫራቾች ናሙናዎቻቸውን ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮዳቸውን ሰጥተው ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም ለአንድ የአቅርቦት ዓይነት አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት (የራሱ ስቶክ) ያለውና፤ እቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) እስከ ሆስፒታሉ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ ማስረከብ አለበት።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ መረጃቸውን እና፤ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት መምጣት ይኖርባቸዋል፤ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት በሆስፒታሉ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አዲስ (በመኪና ፓርኪንግ ያለበት አከባቢ) በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

9. ተጫራቹ የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ የሎት ቁጥሩ፣ አቅራቢው ሰነድ ሲገዛ የተሰጠው ኮድ ፅፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ያልፃፉ ተጫራቾች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ።

10.ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

11.ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ሆስፒታላችን በሰጠው መሙያ ቅጽ ብቻ መሞላት ይኖርባዋል፤ ማንኛውም ስርዝድልዝ፣ማህተም ያልተደረገበት የቀረበ ዋጋ፣ በሆስፒታሉ ዋጋ መሙያ ቅጽ ያልተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።

12.ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ ቤ/ክ 500 ሜትር አለፍ ብሎ እንገኛለን።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0111112056 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-09-25
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 14, 2026)
  • Posted at: 2026-09-14T11:48:25.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders