Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽዳት እቃዎች፣ የጄኔሬተር አመታዊ ሰርቪስ፣ የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ እንቁላል፣ በርበሬ እና የታሸገ የማዕድን ውሃ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1.የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 2. የጄኔሬተር አመታዊ ሰርቪስ፣
  • ሎት 3. የመኪና መለዋወጫ እቃ፣
  • ሎት 4. እንቁላል፣
  • ሎት 5. በርበሬ፣
  • ሎት 6. የታሸገ የማዕድን ውሃ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3.  ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በየሎቱ በመክፈል በዩኒቨርሲቲው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7.  የሚገዙ የዕቃዎችን አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወይም በኦንላይን ከመስከረም 04/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በዩኒቨርሲቲው የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የተገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በዩኒቨርሲቲው ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ04/01/2019 ዓ.ም እስከ 13/01/2019 ዓ.ም 9፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. የጨረታ ሳጥኑ መስከረም 13/2019 ዓ.ም 9፡00 ስዓት ታሽጎ 9፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  12. የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  13.  ዩኒቨርስቲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት
  16.  ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 2360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 የአማራ ክልል ስቴት ዩኒቨርሲቲ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-09-23 15:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Regional State University
  • Bid document price: 500.00 ብር በየሎት
  • Published on: Be'kur (Sep 14, 2026)
  • Posted at: 2026-09-14T12:07:23.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders