Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ስር ላሉት ጽ/ቤቶች 01/19 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዢው መለያ ቁጥር ግልጽ ጨረታ 01/19

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ስር ላሉት ጽ/ቤቶች 01/19 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን፡-

  • ሎት-1 የፅህፈት እቃዎች
  • ሎት-2 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት-3 ፈርኒቸር ጥገና
  • ሎት-4 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  • ሎት 5 ቋሚ እቃ ግዢ
  • ሎት 6 ደንብ ልብስ አገልግሎት
  • ሎት-7 ቋሚ አላቂ እቃዎች
  • ሎት-8 የሽልማትና ስጦታ እቃዎች
  • ሎት-9 ህትመት ስራዎች አገልግሎት
  • ሎት-10 የመስተንግዶ አገልግሎት
  • ሎት-11 የጉልበት አገልግሎት
  • ሎት-12 የጭነት መኪና አገልግሎት
  • ሎት-13 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት

ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል በዚህም መሰረት

1) በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑእና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል።

2) ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር

  • ለሎት 1 ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሎት 2 ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሎት 3 ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሎት 4 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሎት 5 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሎት 6 ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሎት 7 ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 8 ብር 10,0000 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 9 ብር 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 10 (ሀ) ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 10 (ለ) 10,000 (አስር ሺህ ብርብቻ)
  • ሎት 11 (ሀ) ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት 11 (ለ) 10000
  • ሎት 12 ብር 13,000 (አስራ ሶስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ለሎት 13 ብር 13,000 (አስራ ሶስት ሺህ ብር ብቻ) በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 13 ጀሞ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወ/13/ጀ/ፋይናንስ ጽ/ቤትጀሞ አንደኛ በር በሚገኘው ሳባ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 606 ላይ በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4) ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በኦርጅናልና በኮፒ ማስታወቂያው ከወጣበት እለትጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤትቢሮ ቁጥር 606 በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 606 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ታሽጎ ይከፈታል፤ ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት1 ሎት2፣ እና ሎት5 ሎት6 ሎት7፤ ሎት8፤ ሎት9፤ ሎት10፤ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ናቸው፤ በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ ፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6) ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት በፊት እና ከቫትጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

7) የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

8) አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የግዢ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9) መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አሽገው ሲመልሱ ሙሉውን ሰነድ መመለስ እና በሁሉም ገጽ ላይ ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል ።

በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ

አድራሻ ጀሞ አንደኛ በር ሳባ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 606

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀሞ ፋ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-24
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀሞ ፋ/ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 14, 2026)
  • Posted at: 2026-09-14T12:07:27.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders