Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
More tags
Description
የ1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ን/ስ/ላ/ክ/ከ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 01/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን በሎት የተገለጹ እቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1፦ የደንበ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00
- ሎት 2: አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 9,000.00
- ሉት 3:- የህትመት ስራዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 9,000.00
- ሎት 4፦ የጽዳት ዕቃዎች- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000.00
- ሎት 5፦ የተለያዩ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000.00
- ሉት 6፦ ቋሚ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00
- ሎት 7፦ የመኪና ዕቃዎችና ማስጌጫዎች እና የጀነሬተር ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00
- ሎት 8፦ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00
- ሎት 9፡- ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000.00
- ሎት 10፡- የመስተንግዶ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000.00
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1.ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ጋር ተዛማጅ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ።
2.በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የተካተቱ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3.ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።:
4.ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5.ጥቃቅንና አነስተኛ የሆኑ አቅራቢዎች ከተደራጁበት ቦታ ምርት አምርተዉ እሴት የሚጨምሩ መሆናቸዉን የሚገልፅ በመ/ቤቱ ስም የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በተጨማሪ ሌሎች አቅራቢዎች የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም ሎቶች በተናጠል ወይም በድምር ከላይ በተቀመጠዉ መሰረት በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። መሠራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች መፈፀም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
6.የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒው ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን መግባት ይኖርበታል፡፡
7.ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ሙሉ ቀንን ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መክፈቻው ቀን ድረስ ከጀሞ ሚካኤል ወደ ጀርመን አደባባይ በሚወስደው መንገድ ድልድዩን እንደተሻገሩ ፅጌ ወይን ህንፃ ላይ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት አራተኛ (4) ፎቅ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ:: የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ ማቅረብ አለባችሁ::
8.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻዉ በማድረግ ጨረታውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል።ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ግብር በግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
9.ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ እና የታደሰ መታወቂያ መያያዝ አለበት፡፡
10.አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም አሸናፊ ሆኖ የተመረጠዉ አቅራቢ የአሸፈበትን የጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
11.ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸዉ ሎቶች ናሙና ማቅረብ አለባቸዉ የህትመት ስራዎችን መ/ቤቱ ባሳየው ሳምፕል መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር 011-385-44-24/011-369-98-30/011-385-40-53
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-25 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nifas Silk lafto Sub City Small Tax Payers Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 13, 2026)
- Posted at: 2026-09-14T12:41:39.000Z
- Source: 2merkato