Vehicle (garage service)
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች የትናንሽ እና የማሽነሪዎች ብልሽት ሲያጋጥም ሰርቪስ ለማስደረግና ጥገና ለማስደረግ ጋራጆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች የትናንሽ እና የማሽነሪዎች ብልሽት ሲያጋጥም ሰርቪስ ለማስደረግና ጥገና ለማስደረግ ጋራጆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ብቻ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በክፍለ ከተማችን ውስጥ ባሉት ባንኮች በተመሰከረ (CPO) ብቻ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በስንቄ ባንክ አካውንት ቁጥር 1064628071215 የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ በትክክል በመሙላት በታሸገ ፖስታ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይንም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት እስከ 4፡00 ሰነዱን የጨረታ ሳጥን ገብቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. ፅ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ለበለጠ መረጃ የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግዢ ከፍል በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡
የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይንም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት እስከ 4፡00
- Bid opening: 2026-10-05 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይንም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት እስከ 4፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheger City Sululta Sub City Administration FEDB
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 15, 2026)
- Posted at: 2026-09-15T08:14:23.000Z
- Source: 2merkato